-
ዘፍጥረት 9:20, 21አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 ኖኅም ገበሬ ሆነ፤ የወይን እርሻም አለማ። 21 አንድ ቀን ኖኅ የወይን ጠጅ ጠጥቶ ሰከረ፤ በድንኳኑም ውስጥ ራቁቱን ሆነ።
-
-
ምሳሌ 23:29-35አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
29 ዋይታ የማን ነው? ጭንቀት የማን ነው?
ጠብ የማን ነው? እሮሮ የማን ነው?
ያለምክንያት መቁሰል የማን ነው? የዓይን ቅላት* የማን ነው?
31 በብርጭቆ ውስጥ ሲያንጸባርቅ፣
እየጣፈጠም ሲወርድ በወይን ጠጅ ቅላት ዓይንህ አይማረክ፤
32 በመጨረሻ እንደ እባብ ይናደፋልና፤
እንደ እፉኝትም መርዙን ይረጫል።
33 ዓይኖችህ እንግዳ ነገር ያያሉ፤
ልብህም ጠማማ ነገር ይናገራል።+
34 በባሕር መካከል እንደተኛ፣
በመርከብ ምሰሶም ጫፍ ላይ እንደተጋደመ ሰው ትሆናለህ።
35 እንዲህ ትላለህ፦ “መቱኝ፤ ሆኖም አልተሰማኝም።*
ደበደቡኝ፤ ሆኖም አልታወቀኝም።
ተጨማሪ መጠጥ እጠጣ ዘንድ*
የምነቃው መቼ ነው?”+
-