1 ሳሙኤል 20:33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 33 በዚህ ጊዜ ሳኦል እሱን ለመግደል ጦሩን ወረወረበት፤+ ስለሆነም ዮናታን አባቱ፣ ዳዊትን ለመግደል ቆርጦ መነሳቱን አወቀ።+ ምሳሌ 16:32 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 ቶሎ የማይቆጣ ሰው+ ከኃያል ሰው፣ስሜቱን የሚቆጣጠርም* ከተማን ድል ከሚያደርግ ሰው ይሻላል።+ ምሳሌ 22:24, 25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ከግልፍተኛ ሰው ጋር አትግጠም፤በቀላሉ ቱግ ከሚል ሰውም ጋር አትቀራረብ፤25 አለዚያ መንገዱን ትማራለህ፤ለራስህም* ወጥመድ ይሆናል።+ ምሳሌ 29:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ሞኝ ስሜቱን* ሁሉ እንዳሻው ይገልጻል፤+ጥበበኛ ግን ስሜቱን ይቆጣጠራል።+