-
ማቴዎስ 21:23-25አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
23 ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ እያስተማረ ሳለ የካህናት አለቆችና የሕዝቡ ሽማግሌዎች ወደ እሱ መጥተው “እነዚህን ነገሮች የምታደርገው በምን ሥልጣን ነው? ይህን ሥልጣን የሰጠህስ ማን ነው?” አሉት።+ 24 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “እኔም አንድ ነገር እጠይቃችኋለሁ። መልሱን ከነገራችሁኝ እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ እነግራችኋለሁ፦ 25 ዮሐንስ እንዲያጠምቅ ሥልጣን የሰጠው ማን ነው? አምላክ* ነው ወይስ ሰው?” እነሱ ግን እርስ በርሳቸው እንዲህ ይባባሉ ጀመር፦ “‘አምላክ’ ብንል ‘ታዲያ ለምን አላመናችሁትም?’ ይለናል፤+
-