-
ማርቆስ 11:27-33አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
27 እንደገናም ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። በቤተ መቅደሱም ሲዘዋወር የካህናት አለቆች፣ ጸሐፍትና ሽማግሌዎች መጥተው 28 “እነዚህን ነገሮች የምታደርገው በምን ሥልጣን ነው? እነዚህን ነገሮች እንድታደርግስ ሥልጣን የሰጠህ ማን ነው?” አሉት።+ 29 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “አንድ ጥያቄ እጠይቃችኋለሁ። እናንተም መልሱልኝ፤ እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ እነግራችኋለሁ። 30 ዮሐንስ የማጥመቅ ሥልጣን+ ያገኘው ከአምላክ* ነው ወይስ ከሰው? መልሱልኝ።”+ 31 እነሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ይባባሉ ጀመር፦ “‘ከአምላክ’ ብንል ‘ታዲያ ለምን አላመናችሁትም?’ ይለናል፤ 32 ደፍረን ‘ከሰው ነው’ ብንልስ?” ሰዎቹ ሁሉ ዮሐንስን እንደ ነቢይ ያዩት ስለነበር ሕዝቡን ፈሩ።+ 33 ስለዚህ ለኢየሱስ “አናውቅም” ብለው መለሱለት። ኢየሱስም “እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ አልነግራችሁም” አላቸው።
-
-
ሉቃስ 20:1-8አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 አንድ ቀን ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ሕዝቡን እያስተማረና ምሥራቹን እያወጀ ሳለ የካህናት አለቆችና ጸሐፍት ከሕዝቡ ሽማግሌዎች ጋር መጡ፤ 2 ከዚያም “እስቲ ንገረን፤ እነዚህን ነገሮች የምታደርገው በምን ሥልጣን ነው? ይህን ሥልጣን የሰጠህስ ማን ነው?” አሉት።+ 3 እሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “እኔም አንድ ጥያቄ እጠይቃችኋለሁ፤ እናንተም መልሱልኝ፦ 4 ዮሐንስ የማጥመቅ ሥልጣን ያገኘው ከአምላክ* ነው ወይስ ከሰው?” 5 እነሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፦ “‘ከአምላክ’ ብንል ‘ታዲያ ለምን አላመናችሁትም?’ ይለናል፤ 6 ‘ከሰው’ ብንል ደግሞ ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስ ነቢይ ነው ብለው ስለሚያምኑ+ በድንጋይ ይወግሩናል።” 7 ስለዚህ ‘ከየት እንደሆነ አናውቅም’ ብለው መለሱለት። 8 ኢየሱስም “እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ አልነግራችሁም” አላቸው።
-