-
ማቴዎስ 21:23-27አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
23 ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ እያስተማረ ሳለ የካህናት አለቆችና የሕዝቡ ሽማግሌዎች ወደ እሱ መጥተው “እነዚህን ነገሮች የምታደርገው በምን ሥልጣን ነው? ይህን ሥልጣን የሰጠህስ ማን ነው?” አሉት።+ 24 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “እኔም አንድ ነገር እጠይቃችኋለሁ። መልሱን ከነገራችሁኝ እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ እነግራችኋለሁ፦ 25 ዮሐንስ እንዲያጠምቅ ሥልጣን የሰጠው ማን ነው? አምላክ* ነው ወይስ ሰው?” እነሱ ግን እርስ በርሳቸው እንዲህ ይባባሉ ጀመር፦ “‘አምላክ’ ብንል ‘ታዲያ ለምን አላመናችሁትም?’ ይለናል፤+ 26 ‘ሰው’ ብንል ደግሞ ዮሐንስን ሁሉም እንደ ነቢይ ስለሚያየው ሕዝቡን እንፈራለን።” 27 ስለዚህ ለኢየሱስ “አናውቅም” ብለው መለሱለት። እሱ ደግሞ እንዲህ አላቸው፦ “እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ አልነግራችሁም።
-
-
ማርቆስ 11:27-33አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
27 እንደገናም ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። በቤተ መቅደሱም ሲዘዋወር የካህናት አለቆች፣ ጸሐፍትና ሽማግሌዎች መጥተው 28 “እነዚህን ነገሮች የምታደርገው በምን ሥልጣን ነው? እነዚህን ነገሮች እንድታደርግስ ሥልጣን የሰጠህ ማን ነው?” አሉት።+ 29 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “አንድ ጥያቄ እጠይቃችኋለሁ። እናንተም መልሱልኝ፤ እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ እነግራችኋለሁ። 30 ዮሐንስ የማጥመቅ ሥልጣን+ ያገኘው ከአምላክ* ነው ወይስ ከሰው? መልሱልኝ።”+ 31 እነሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ይባባሉ ጀመር፦ “‘ከአምላክ’ ብንል ‘ታዲያ ለምን አላመናችሁትም?’ ይለናል፤ 32 ደፍረን ‘ከሰው ነው’ ብንልስ?” ሰዎቹ ሁሉ ዮሐንስን እንደ ነቢይ ያዩት ስለነበር ሕዝቡን ፈሩ።+ 33 ስለዚህ ለኢየሱስ “አናውቅም” ብለው መለሱለት። ኢየሱስም “እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ አልነግራችሁም” አላቸው።
-