ዘፀአት 7:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ይሁንና አስማት የሚሠሩ የግብፅ ካህናትም በሚስጥራዊ ጥበባቸው ተመሳሳይ ነገር አደረጉ፤+ በመሆኑም የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ ልክ ይሖዋ እንዳለውም እነሱን ለመስማት እንቢተኛ ሆነ።+ ነህምያ 9:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 ወደ ሕግህ እንዲመለሱ ለማድረግ ብታስጠነቅቃቸውም እነሱ ግን እብሪተኞች በመሆን ትእዛዛትህን ለመስማት አሻፈረኝ አሉ፤+ ለሚጠብቃቸው ሰው ሁሉ ሕይወት በሚያስገኙት ድንጋጌዎችህ ላይ ኃጢአት ሠሩ።+ ደግሞም በግትርነት ጀርባቸውን ሰጡ፤ አንገታቸውን አደነደኑ፤ ለመስማትም አሻፈረኝ አሉ። ምሳሌ 29:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 ብዙ ጊዜ ተወቅሶ አንገቱን ያደነደነ* ሰው፣+ሊፈወስ በማይችል ሁኔታ በድንገት ይሰበራል።+ ኤርምያስ 16:12, 13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 እናንተ ደግሞ አባቶቻችሁ ከፈጸሙት የባሰ ነገር አድርጋችኋል፤+ እያንዳንዳችሁም እኔን ከመታዘዝ ይልቅ ግትር የሆነውን ክፉ ልባችሁን ተከተላችሁ።+ 13 ስለዚህ ከዚህች ምድር አስወጥቼ እናንተም ሆነ አባቶቻችሁ ወደማታውቁት ምድር እጥላችኋለሁ፤+ በዚያም ሌሎች አማልክትን ቀን ከሌት ታገለግላላችሁ፤+ ምክንያቱም እኔ ምንም ምሕረት አላሳያችሁም።”’
22 ይሁንና አስማት የሚሠሩ የግብፅ ካህናትም በሚስጥራዊ ጥበባቸው ተመሳሳይ ነገር አደረጉ፤+ በመሆኑም የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ ልክ ይሖዋ እንዳለውም እነሱን ለመስማት እንቢተኛ ሆነ።+
29 ወደ ሕግህ እንዲመለሱ ለማድረግ ብታስጠነቅቃቸውም እነሱ ግን እብሪተኞች በመሆን ትእዛዛትህን ለመስማት አሻፈረኝ አሉ፤+ ለሚጠብቃቸው ሰው ሁሉ ሕይወት በሚያስገኙት ድንጋጌዎችህ ላይ ኃጢአት ሠሩ።+ ደግሞም በግትርነት ጀርባቸውን ሰጡ፤ አንገታቸውን አደነደኑ፤ ለመስማትም አሻፈረኝ አሉ።
12 እናንተ ደግሞ አባቶቻችሁ ከፈጸሙት የባሰ ነገር አድርጋችኋል፤+ እያንዳንዳችሁም እኔን ከመታዘዝ ይልቅ ግትር የሆነውን ክፉ ልባችሁን ተከተላችሁ።+ 13 ስለዚህ ከዚህች ምድር አስወጥቼ እናንተም ሆነ አባቶቻችሁ ወደማታውቁት ምድር እጥላችኋለሁ፤+ በዚያም ሌሎች አማልክትን ቀን ከሌት ታገለግላላችሁ፤+ ምክንያቱም እኔ ምንም ምሕረት አላሳያችሁም።”’