-
2 ነገሥት 5:20-22አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 የእውነተኛው አምላክ ሰው+ የኤልሳዕ አገልጋይ የሆነው ግያዝ+ ‘ጌታዬ ሶርያዊው ንዕማን+ ያመጣውን ነገር ሳይቀበለው እንዲሁ አሰናበተው። ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣ ተከትዬው ሮጬ የሆነ ነገር እቀበለዋለሁ’ ብሎ አሰበ። 21 ስለዚህ ግያዝ ንዕማንን ተከተለው። ንዕማንም አንድ ሰው በሩጫ እየተከተለው እንዳለ ሲያይ ሰውየውን ለማግኘት ከሠረገላው ላይ ወርዶ “በደህና ነው?” አለው። 22 በዚህ ጊዜ ግያዝ እንዲህ አለው፦ “አዎ፣ በደህና ነው። ጌታዬ ‘ከነቢያት ልጆች መካከል ሁለት ወጣቶች ከተራራማው ከኤፍሬም አካባቢ አሁን ድንገት ወደ እኔ መጡ። ስለሆነም እባክህ አንድ ታላንት ብርና ሁለት ቅያሪ ልብስ ስጣቸው’+ ብዬ እንድነግርህ ልኮኝ ነው።”
-
-
ኤርምያስ 17:11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
በዕድሜው አጋማሽ ላይ ሀብቱ ትቶት ይሄዳል፤
በመጨረሻም የማመዛዘን ችሎታ የጎደለው ሰው መሆኑ ይረጋገጣል።”
-