-
መክብብ 2:2, 3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
2 ሳቅ “እብደት ነው!”
ደስታም “ምን ይጠቅማል?” አልኩ።
3 በገዛ ጥበቤ እየተመራሁና ራሴን በወይን ጠጅ እያስደሰትኩ+ በጥልቀት መረመርኩ፤ ሰዎች አጭር በሆነው የሕይወት ዘመናቸው ከሰማይ በታች ሊያደርጉት የሚችሉት ከሁሉ የተሻለ ነገር ምን እንደሆነ ለማወቅ በሞኝነት እንኳ ሳይቀር ተመላለስኩ።
-
-
መክብብ 2:12አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
12 ከዚያም ትኩረቴን ወደ ጥበብ፣ እብደትና ሞኝነት አዞርኩ።+ (ከንጉሥ በኋላ የሚመጣው ሰው ምን ሊያደርግ ይችላል? ሊያደርግ የሚችለው ቀደም ሲል የተደረገውን ነገር ብቻ ነው።)
-
-
መክብብ 7:25አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
25 እኔም ጥበብንና የነገሮችን መንስኤ ለመረዳት፣ ለመመርመርና ለማጥናት እንዲሁም የሞኝነትን ክፋትና የእብደትን ቂልነት ለመገንዘብ ልቤን አዘነበልኩ።+
-