ኢዮብ 7:9, 10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 እንደሚበተንና እንደሚጠፋ ደመና፣ወደ መቃብር* የሚወርድም ተመልሶ አይወጣም።+ 10 ዳግመኛ ወደ ቤቱ አይመለስም፤ስፍራውም ከእንግዲህ ወዲህ አያውቀውም።+ መክብብ 2:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ጥበበኛውም ሆነ ሞኙ ለዘለቄታው አይታወሱምና።+ ሁሉም በሚመጡት ዘመናት ይረሳሉ። ለመሆኑ ጥበበኛው የሚሞተው እንዴት ነው? ልክ እንደ ሞኙ ሰው ይሞታል።+