2 ጻድቁና ክፉው ሰው፣+ ጥሩው ሰውም ሆነ ንጹሕ የሆነውና ንጹሕ ያልሆነው ሰው፣ መሥዋዕት የሚያቀርቡትም ሆኑ የማያቀርቡት ፍጻሜያቸው ተመሳሳይ ነው።+ ጥሩው ሰው ከኃጢአተኛው ጋር አንድ ነው፤ የሚምለውም ሰው፣ ላለመማል ከሚጠነቀቀው ሰው ጋር አንድ ነው። 3 ከፀሐይ በታች የሚፈጸመው አስጨናቂ ነገር ይህ ነው፦ የሁሉም ፍጻሜ አንድ ስለሆነ+ የሰዎችም ልብ በክፋት የተሞላ ነው፤ በሕይወታቸው ዘመን በልባቸው ውስጥ እብደት አለ፤ ከዚያም ይሞታሉ!