-
መክብብ 2:4-8አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 ታላላቅ ሥራዎችን አከናወንኩ።+ ለራሴ ቤቶችን ሠራሁ፤+ ወይንም ተከልኩ።+ 5 ለራሴ የአትክልት ስፍራዎችንና መናፈሻዎችን አዘጋጀሁ፤ በእነዚህም ቦታዎች ሁሉንም ዓይነት የፍራፍሬ ዛፎች ተከልኩ። 6 በእርሻው መሬት ላይ እያደጉ ያሉትን ዛፎች* ለማጠጣት የውኃ ማጠራቀሚያዎችን ሠራሁ። 7 ወንድና ሴት አገልጋዮች አስመጣሁ፤+ በቤቴ የተወለዱ አገልጋዮችም* ነበሩኝ። በተጨማሪም ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይበልጥ ብዛት ያላቸው እንስሶች፣ ከብቶችና መንጎች ነበሩኝ።+ 8 ለራሴም ብርና ወርቅ፣+ የነገሥታትንና የአውራጃዎችን ውድ ሀብት* አከማቸሁ።+ ወንድና ሴት ዘፋኞችን እንዲሁም የሰው ልጆች እጅግ የሚደሰቱባቸውን ብዙ ሴቶች* ሰበሰብኩ።
-