-
1 ሳሙኤል 19:4አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 በመሆኑም ዮናታን ለአባቱ ለሳኦል ስለ ዳዊት መልካም ነገር ነገረው።+ እንዲህም አለው፦ “ንጉሡ በአገልጋዩ በዳዊት ላይ ኃጢአት አይሥራ፤ ምክንያቱም እሱ በአንተ ላይ የሠራው ኃጢአት የለም፤ ያደረገልህም ነገር ቢሆን ለአንተ የሚበጅ ነው።
-
-
1 ሳሙኤል 25:23, 24አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
23 አቢጋኤልም ዳዊትን ባየችው ጊዜ፣ ከተቀመጠችበት አህያ ላይ በፍጥነት በመውረድ በዳዊት ፊት በግንባሯ ተደፍታ ሰገደች። 24 ከዚያም እግሩ ላይ ወድቃ እንዲህ አለችው፦ “ጌታዬ ሆይ፣ ጥፋቱ በእኔ ላይ ይሁን፤ እባክህ አገልጋይህ እንድታናግርህ ፍቀድላት፤ የአገልጋይህንም ቃል ስማ።
-