4 “ፍቅሬ ሆይ፣ እነሆ፣ አንቺ ውብ ነሽ።
እነሆ፣ አንቺ ውብ ነሽ።
ዓይኖችሽ በፊትሽ መሸፈኛ ውስጥ ሲታዩ እንደ ርግብ ዓይኖች ናቸው።
ፀጉርሽ ከጊልያድ+ ተራሮች
እየተግተለተለ እንደሚወርድ የፍየል መንጋ ነው።
2 ጥርሶችሽ ገና ተሸልተውና
ታጥበው እንደወጡ፣
ሁሉም መንታ መንታ እንደወለዱ የበግ መንጋ ናቸው፤
ደግሞም ከመካከላቸው ግልገሉን ያጣ የለም።
3 ከንፈሮችሽ እንደ ደማቅ ቀይ ፈትል ናቸው፤
ንግግርሽም አስደሳች ነው።
በመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ጉንጮችሽ
የተከፈለ ሮማን ይመስላሉ።