ዘፀአት 13:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ይሖዋ የሚሄዱበትን መንገድ ይመራቸው ዘንድ ቀን ቀን በደመና ዓምድ ውስጥ ሆኖ ከፊት ከፊታቸው ይሄድ ነበር፤+ ሌሊት ሌሊት ደግሞ ብርሃን እንዲያገኙ ለማድረግ በእሳት ዓምድ ውስጥ ሆኖ ይመራቸው ነበር፤+ በመሆኑም ቀንም ሆነ ሌሊት ይጓዙ ነበር። ዘኁልቁ 9:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 የማደሪያ ድንኳኑ በተተከለበት ቀን+ ደመናው የማደሪያ ድንኳኑን ይኸውም የምሥክሩን ድንኳን ሸፈነው፤ ሆኖም ከምሽት ጀምሮ እስከ ጠዋት ድረስ በማደሪያ ድንኳኑ ላይ እሳት የሚመስል ነገር ታየ።+ ዘካርያስ 2:4, 5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ከዚያም እንዲህ አለው፦ “ወደዚያ ሮጠህ ሂድና ያንን ወጣት እንዲህ በለው፦ ‘“በመካከሏ ካሉት ሰዎችና መንጎች ሁሉ የተነሳ+ ኢየሩሳሌም ቅጥር እንደሌላቸው መንደሮች በነዋሪዎች ትሞላለች።+ 5 እኔም በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ”+ ይላል ይሖዋ፤ “ክብሬም በመካከሏ ይሆናል።”’”+
21 ይሖዋ የሚሄዱበትን መንገድ ይመራቸው ዘንድ ቀን ቀን በደመና ዓምድ ውስጥ ሆኖ ከፊት ከፊታቸው ይሄድ ነበር፤+ ሌሊት ሌሊት ደግሞ ብርሃን እንዲያገኙ ለማድረግ በእሳት ዓምድ ውስጥ ሆኖ ይመራቸው ነበር፤+ በመሆኑም ቀንም ሆነ ሌሊት ይጓዙ ነበር።
15 የማደሪያ ድንኳኑ በተተከለበት ቀን+ ደመናው የማደሪያ ድንኳኑን ይኸውም የምሥክሩን ድንኳን ሸፈነው፤ ሆኖም ከምሽት ጀምሮ እስከ ጠዋት ድረስ በማደሪያ ድንኳኑ ላይ እሳት የሚመስል ነገር ታየ።+
4 ከዚያም እንዲህ አለው፦ “ወደዚያ ሮጠህ ሂድና ያንን ወጣት እንዲህ በለው፦ ‘“በመካከሏ ካሉት ሰዎችና መንጎች ሁሉ የተነሳ+ ኢየሩሳሌም ቅጥር እንደሌላቸው መንደሮች በነዋሪዎች ትሞላለች።+ 5 እኔም በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ”+ ይላል ይሖዋ፤ “ክብሬም በመካከሏ ይሆናል።”’”+