-
ሉቃስ 4:17-21አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 የነቢዩ ኢሳይያስ ጥቅልልም ተሰጠው፤ ጥቅልሉንም ተርትሮ እንዲህ ተብሎ የተጻፈበትን ቦታ አገኘ፦ 18 “የይሖዋ* መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ምክንያቱም ለድሆች ምሥራች እንድናገር ቀብቶኛል። ለተማረኩት ነፃነትን፣ ለታወሩትም ማየትን እንዳውጅ፣ የተጨቆኑትን ነፃ እንዳወጣ+ 19 እንዲሁም የይሖዋን* ሞገስ ስለሚያገኙበት ዓመት+ እንድሰብክ ልኮኛል።” 20 ከዚያም ጥቅልሉን ጠቅልሎ ለአገልጋዩ መልሶ ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኩራቡ ውስጥ ያሉት ሰዎችም ሁሉ ትኩር ብለው ይመለከቱት ነበር። 21 እሱም “ይህ አሁን የሰማችሁት የቅዱሳን መጻሕፍት ቃል ዛሬ ተፈጸመ” አላቸው።+
-