14 ይሖዋ ለያዕቆብ ምሕረት ያሳያልና፤+ እስራኤልንም እንደገና ይመርጠዋል።+ በምድራቸው ላይ ያሰፍራቸዋል፤+ የባዕድ አገር ሰዎችም ከእነሱ ጋር ይሆናሉ፤ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይጣበቃሉ።+ 2 ሕዝቦችም ይወስዷቸዋል፤ ወደ ገዛ ስፍራቸውም ይመልሷቸዋል፤ የእስራኤልም ቤት በይሖዋ ምድር ላይ ወንድና ሴት አገልጋዮቻቸው ያደርጓቸዋል፤+ ማርከው የወሰዷቸውንም ይማርካሉ፤ አስገድደው ያሠሯቸው የነበሩትንም ይገዟቸዋል።