ኢሳይያስ 56:6, 7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 እሱን ለማገልገል፣ የይሖዋን ስም ለመውደድናየእሱ አገልጋዮች ለመሆንከይሖዋ ጋር የሚቆራኙትን የባዕድ አገር ሰዎች፣+ሰንበትን የሚጠብቁትንና የማያረክሱትን፣ቃል ኪዳኔንም አጥብቀው የሚይዙትን ሁሉ፣ 7 ቅዱስ ወደሆነው ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፤+በጸሎት ቤቴም ውስጥ እጅግ እንዲደሰቱ አደርጋቸዋለሁ። የሚያቀርቧቸውም ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችና መሥዋዕቶች በመሠዊያዬ ላይ ተቀባይነት ያገኛሉ። ቤቴም ለሕዝቦች ሁሉ የጸሎት ቤት ተብሎ ይጠራልና።”+ ኢሳይያስ 60:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ብሔራት ወደ ብርሃንሽ፣+ነገሥታትም+ አንጸባራቂ ወደሆነው ውበትሽ* ይመጣሉ።+ ዘካርያስ 8:22, 23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ደግሞም ብዙ ሕዝቦችና ኃያላን ብሔራት የሠራዊት ጌታ ይሖዋን ለመፈለግና ይሖዋ ሞገሱን እንዲያሳያቸው ለመለመን ወደ ኢየሩሳሌም ይመጣሉ።’+ 23 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዚያን ጊዜ ከብሔራት ቋንቋዎች ሁሉ የተውጣጡ+ አሥር ሰዎች የአንድን አይሁዳዊ ልብስ* አጥብቀው በመያዝ “አምላክ ከእናንተ ጋር መሆኑን ስለሰማን ከእናንተ ጋር እንሄዳለን”+ ይላሉ።’”+
6 እሱን ለማገልገል፣ የይሖዋን ስም ለመውደድናየእሱ አገልጋዮች ለመሆንከይሖዋ ጋር የሚቆራኙትን የባዕድ አገር ሰዎች፣+ሰንበትን የሚጠብቁትንና የማያረክሱትን፣ቃል ኪዳኔንም አጥብቀው የሚይዙትን ሁሉ፣ 7 ቅዱስ ወደሆነው ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፤+በጸሎት ቤቴም ውስጥ እጅግ እንዲደሰቱ አደርጋቸዋለሁ። የሚያቀርቧቸውም ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችና መሥዋዕቶች በመሠዊያዬ ላይ ተቀባይነት ያገኛሉ። ቤቴም ለሕዝቦች ሁሉ የጸሎት ቤት ተብሎ ይጠራልና።”+
22 ደግሞም ብዙ ሕዝቦችና ኃያላን ብሔራት የሠራዊት ጌታ ይሖዋን ለመፈለግና ይሖዋ ሞገሱን እንዲያሳያቸው ለመለመን ወደ ኢየሩሳሌም ይመጣሉ።’+ 23 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዚያን ጊዜ ከብሔራት ቋንቋዎች ሁሉ የተውጣጡ+ አሥር ሰዎች የአንድን አይሁዳዊ ልብስ* አጥብቀው በመያዝ “አምላክ ከእናንተ ጋር መሆኑን ስለሰማን ከእናንተ ጋር እንሄዳለን”+ ይላሉ።’”+