-
ዘፀአት 9:15, 16አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
15 እስካሁን እጄን ዘርግቼ አንተንም ሆነ ሕዝብህን አጥፊ በሆነ መቅሰፍት በመታኋችሁ ነበር፤ አንተም ከምድር ገጽ ተጠራርገህ በጠፋህ ነበር። 16 ሆኖም ኃይሌን እንዳሳይህና ስሜ በመላው ምድር እንዲታወጅ ስል በሕይወት አቆይቼሃለሁ።+
-
-
ዘፀአት 14:17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 እኔ ደግሞ የግብፃውያን ልብ እንዲደነድን ስለምፈቅድ እስራኤላውያንን ተከትለው ይገባሉ፤ እኔም ፈርዖንን፣ ሠራዊቱን ሁሉ፣ የጦር ሠረገሎቹንና ፈረሰኞቹን ድል በማድረግ ለራሴ ክብርን እጎናጸፋለሁ።+
-
-
ሮም 9:17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 ቅዱስ መጽሐፉ ስለ ፈርዖን ሲናገር “በሕይወት ያቆየሁህ ኃይሌን በአንተ ለማሳየትና ስሜ በመላው ምድር እንዲታወጅ ለማድረግ ነው” ይላል።+
-