2 ነገሥት 18:13, 14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ንጉሥ ሕዝቅያስ በነገሠ በ14ኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም+ በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ላይ ዘምቶ ያዛቸው።+ 14 በመሆኑም የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ በለኪሶ ወደነበረው ወደ አሦር ንጉሥ “በድያለሁ። እባክህ ከእኔ ተመለስ፤ እኔም የምትጠይቀኝን ነገር ሁሉ እሰጣለሁ” የሚል መልእክት ላከ። የአሦርም ንጉሥ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ላይ 300 የብር ታላንትና* 30 የወርቅ ታላንት ቅጣት ጣለበት። 2 ዜና መዋዕል 28:19, 20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ይሖዋ በእስራኤል ንጉሥ በአካዝ የተነሳ ይሁዳን አዋረደ፤ ምክንያቱም አካዝ የይሁዳን ሰዎች መረን ለቆ ነበር፤ ይህም ንጉሡ ለይሖዋ የነበረውን ታማኝነት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያጓድል አደረገው። 20 በመጨረሻም የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር+ እሱን ከመርዳት ይልቅ በእሱ ላይ ዘምቶ አስጨነቀው።+ ኢሳይያስ 36:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 36 ንጉሥ ሕዝቅያስ በነገሠ በ14ኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ+ ሰናክሬም በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ላይ ዘምቶ ያዛቸው።+
13 ንጉሥ ሕዝቅያስ በነገሠ በ14ኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም+ በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ላይ ዘምቶ ያዛቸው።+ 14 በመሆኑም የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ በለኪሶ ወደነበረው ወደ አሦር ንጉሥ “በድያለሁ። እባክህ ከእኔ ተመለስ፤ እኔም የምትጠይቀኝን ነገር ሁሉ እሰጣለሁ” የሚል መልእክት ላከ። የአሦርም ንጉሥ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ላይ 300 የብር ታላንትና* 30 የወርቅ ታላንት ቅጣት ጣለበት።
19 ይሖዋ በእስራኤል ንጉሥ በአካዝ የተነሳ ይሁዳን አዋረደ፤ ምክንያቱም አካዝ የይሁዳን ሰዎች መረን ለቆ ነበር፤ ይህም ንጉሡ ለይሖዋ የነበረውን ታማኝነት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያጓድል አደረገው። 20 በመጨረሻም የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር+ እሱን ከመርዳት ይልቅ በእሱ ላይ ዘምቶ አስጨነቀው።+