የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማቴዎስ 4:13-16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ከዚያም ከናዝሬት ወጥቶ በዛብሎንና በንፍታሌም አውራጃዎች፣ በባሕሩ* አጠገብ ወደምትገኘው ወደ ቅፍርናሆም+ መጥቶ መኖር ጀመረ፤ 14 ይህም የሆነው በነቢዩ ኢሳይያስ የተነገረው የሚከተለው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው፦ 15 “ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ ወደ ባሕሩ* በሚወስደው መንገድ አጠገብ ያላችሁ የዛብሎን ምድር፣ የንፍታሌም ምድርና የአሕዛብ ገሊላ ሆይ! 16 በጨለማ ውስጥ ያሉ ሰዎች ታላቅ ብርሃን አዩ፤ ሞት በሰዎች ላይ ባጠላበት ምድር ላሉም ብርሃን+ ወጣላቸው።”+

  • ሉቃስ 1:78, 79
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 78 ይህም የሆነው አምላካችን ከአንጀት ስለራራልን ነው። ከዚህ ርኅራኄም የተነሳ እንደ ንጋት ፀሐይ የሚያበራ ብርሃን ከላይ ይወጣልናል፤ 79 ይኸውም በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ+ ለተቀመጡት ብርሃን ለመስጠት እንዲሁም እግሮቻችንን በሰላም መንገድ ለመምራት ነው።”

  • ሉቃስ 2:30-32
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 30 ምክንያቱም ዓይኖቼ ሰዎችን የምታድንበትን መንገድ አይተዋል፤+ 31 ይህም በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸው ነው፤+ 32 ደግሞም ብሔራትን የጋረደውን መሸፈኛ+ የሚገልጥ ብርሃን+ እንዲሁም የሕዝብህ የእስራኤል ክብር ነው።”

  • ዮሐንስ 1:9
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 9 ለሁሉም ዓይነት ሰው ብርሃን የሚሰጠው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም የሚመጣበት ጊዜ ደርሶ ነበር።+

  • ዮሐንስ 8:12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 8 12 ደግሞም ኢየሱስ ሰዎቹን እንዲህ አላቸው፦ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ።+ እኔን የሚከተል ሁሉ በምንም ዓይነት በጨለማ አይሄድም፤ ከዚህ ይልቅ የሕይወት ብርሃን ያገኛል።”+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ