25 “ልጆችና የልጅ ልጆች ስታፈሩ፣ በምድሪቱም ላይ ረጅም ዘመን ስትኖሩ፣ የጥፋት ጎዳና ወደመከተል ዞር ብትሉና የማንኛውንም ነገር የተቀረጸ ምስል+ ብትሠሩ እንዲሁም በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ክፉ ነገር በመፈጸም እሱን ብታስቆጡት+ 26 ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ከምትወርሷት ምድር ያለጥርጥር ወዲያውኑ እንደምትደመሰሱ በዚህ ቀን ሰማይንና ምድርን በእናንተ ላይ ምሥክር አድርጌ እጠራባችኋለሁ። በምድሪቱ ላይ ረጅም ዘመን ከመኖር ይልቅ ሙሉ በሙሉ ትደመሰሳላችሁ።+