-
ኤርምያስ 4:19አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
19 ወይ አበሳዬ!* ወይ አበሳዬ!
ልቤን ሥቃይ ቀስፎታል።
ልቤ በውስጤ በኃይል ይመታል።
-
-
ኤርምያስ 8:18, 19አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
18 ማጽናኛ የማይገኝለት ሐዘን ደርሶብኛል፤
ልቤ ታሟል።
19 የሕዝቤ ሴት ልጅ “ይሖዋ በጽዮን የለም?
ወይስ ንጉሧ በዚያ የለም?”
የሚል የእርዳታ ጥሪ
ከሩቅ አገር ታሰማለች።
“በተቀረጹት ምስሎቻቸውና
ከንቱ በሆኑት ባዕዳን አማልክታቸው ያስከፉኝ ለምንድን ነው?”
-
-
ኤርምያስ 9:1አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
9 ምነው ራሴ በውኃ በተሞላ!
ዓይኖቼ የእንባ ምንጭ በሆኑ!+
ለታረዱት ወገኖቼ
ቀን ከሌት ባለቀስኩ ነበር።
-