ዘዳግም 28:63, 64 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 63 “ይሖዋ እናንተን በማበልጸግና በማብዛት እጅግ ይደሰት እንደነበረው ሁሉ ይሖዋ እናንተን በማጥፋትና በመደምሰስም እጅግ ይደሰታል፤ ገብታችሁ ከምትወርሷት ምድር ላይ ተጠራርጋችሁ ትጠፋላችሁ። 64 “ይሖዋ ከአንዱ የምድር ጫፍ እስከ ሌላኛው የምድር ጫፍ በብሔራት ሁሉ መካከል ይበትንሃል፤+ እዚያም አንተም ሆንክ አባቶችህ የማታውቋቸውን ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ አማልክት ታገለግላለህ።+ ነህምያ 1:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 “እባክህ አገልጋይህን ሙሴን እንዲህ በማለት ያዘዝከውን ቃል* አስታውስ፦ ‘ታማኝነት የጎደለው ድርጊት የምትፈጽሙ ከሆነ በሕዝቦች መካከል እበትናችኋለሁ።+ ኤርምያስ 9:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 እነሱም ሆኑ አባቶቻቸው በማያውቋቸው ብሔራት መካከል እበትናቸዋለሁ፤+ ሙሉ በሙሉ እስካጠፋቸውም ድረስ ከኋላቸው ሰይፍን እሰዳለሁ።’+
63 “ይሖዋ እናንተን በማበልጸግና በማብዛት እጅግ ይደሰት እንደነበረው ሁሉ ይሖዋ እናንተን በማጥፋትና በመደምሰስም እጅግ ይደሰታል፤ ገብታችሁ ከምትወርሷት ምድር ላይ ተጠራርጋችሁ ትጠፋላችሁ። 64 “ይሖዋ ከአንዱ የምድር ጫፍ እስከ ሌላኛው የምድር ጫፍ በብሔራት ሁሉ መካከል ይበትንሃል፤+ እዚያም አንተም ሆንክ አባቶችህ የማታውቋቸውን ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ አማልክት ታገለግላለህ።+