ዘኁልቁ 34:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 “ለእስራኤላውያን ይህን መመሪያ ስጣቸው፦ ‘ወደ ከነአን ምድር ስትገቡ+ ርስት አድርጋችሁ የምትወርሷት ምድር ይኸውም የከነአን ምድር ከነወሰኖቿ ይህች ናት።+ ዘኁልቁ 34:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ወሰኑ አጽሞን ላይ ሲደርስ አቅጣጫውን ቀይሮ ወደ ግብፅ ደረቅ ወንዝ* ይሄዳል፤ መጨረሻውም ባሕሩ* ይሆናል።+