የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 29:18
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 18 በዚያ ቀን፣ መስማት የተሳናቸው ሰዎች የመጽሐፉን ቃል ይሰማሉ፤

      የዓይነ ስውራኑም ዓይኖች ከጭጋግና ከጨለማ ተላቀው ያያሉ።+

  • ኤርምያስ 6:10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 “ለማን ልናገር? ማንን ላስጠንቅቅ?

      ማንስ ይሰማል?

      እነሆ፣ ጆሮዎቻቸው ስለተዘጉ* ማዳመጥ አይችሉም።+

      እነሆ፣ የይሖዋን ቃል መሳለቂያ አድርገውታል፤+

      ቃሉም ደስ አያሰኛቸውም።

  • ማርቆስ 7:32-35
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 32 በዚያም* ሰዎች መስማት የተሳነውና የመናገር እክል ያለበት+ አንድ ሰው ወደ እሱ አምጥተው እጁን እንዲጭንበት ተማጸኑት። 33 እሱም ከሕዝቡ ለይቶ ለብቻው ወሰደው። ከዚያም ጣቶቹን በሰውየው ጆሮዎች ውስጥ አስገባ፤ እንትፍ ካለ በኋላም የሰውየውን ምላስ ዳሰሰ።+ 34 ወደ ሰማይ እየተመለከተም በረጅሙ ተንፍሶ “ኤፈታ” አለው፤ ይህም “ተከፈት” ማለት ነው። 35 በዚህ ጊዜ ጆሮዎቹ ተከፈቱ፤+ ምላሱም ተፈቶ አጥርቶ መናገር ጀመረ።

  • ሉቃስ 7:22
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 22 እሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ሄዳችሁ የሰማችሁትንና ያያችሁትን ነገር ለዮሐንስ ንገሩት፦ ዓይነ ስውሮች እያዩ ነው፤+ አንካሶች እየተራመዱ ነው፤ የሥጋ ደዌ የያዛቸው እየነጹ ነው፤ መስማት የተሳናቸው እየሰሙ ነው፤+ ሙታን እየተነሱ ነው፤ ድሆችም ምሥራቹ እየተነገራቸው ነው።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ