12 ይሖዋ አሞራውያንን ከእስራኤላውያን ፊት ባባረረበት ዕለት ኢያሱ በእስራኤላውያን ፊት ይሖዋን እንዲህ አለው፦
“ፀሐይ ሆይ፣ በገባኦን ላይ ቁሚ፤+
አንቺም ጨረቃ ሆይ፣ በአይሎን ሸለቆ ላይ ቀጥ በይ!”
13 በመሆኑም ብሔሩ ጠላቶቹን እስኪበቀል ድረስ ፀሐይ ባለችበት ቆመች፤ ጨረቃም አልተንቀሳቀሰችም። ይህስ በያሻር መጽሐፍ+ ላይ ተጽፎ የሚገኝ አይደለም? ፀሐይ በሰማይ መካከል ባለችበት ቆመች፤ ለአንድ ቀን ያህል ለመጥለቅ አልቸኮለችም።