1 ሳሙኤል 2:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ይሖዋ ይገድላል፤ ሕይወትንም ያድናል፤*ወደ መቃብር* ያወርዳል፤ ከዚያም ያወጣል።+ ኢዮብ 33:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 እሱ ነፍሴን* ወደ ጉድጓድ* ከመውረድ ታድጓታል፤+ሕይወቴም ብርሃን ታያለች።’ መዝሙር 71:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ብዙ ጭንቅና መከራ ብታሳየኝም እንኳ+እንደገና እንዳንሰራራ አድርገኝ፤ጥልቅ ከሆነው ምድር* አውጣኝ።+