2 ዜና መዋዕል 36:15, 16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 የአባቶቻቸው አምላክ ይሖዋ ለሕዝቡና ለማደሪያው ስፍራ ስለራራ መልእክተኞቹን እየላከ በተደጋጋሚ ያስጠነቅቃቸው ነበር። 16 እነሱ ግን የይሖዋ ቁጣ በሕዝቡ ላይ እስኪነድና+ ፈውስ እስከማይገኝላቸው ድረስ በእውነተኛው አምላክ መልእክተኞች ላይ ያላግጡ፣+ ቃሉን ይንቁና+ በነቢያቱ ላይ ያፌዙ+ ነበር። ነህምያ 9:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 “ይሁንና ለመታዘዝ እንቢተኞች በመሆን በአንተ ላይ ዓመፁ፤+ ለሕግህም ጀርባቸውን ሰጡ።* ወደ አንተ እንዲመለሱ ሲያስጠነቅቋቸው የነበሩትን ነቢያትህን ገደሉ፤ ከፍተኛ ንቀት የሚንጸባረቅባቸውንም ተግባሮች ፈጸሙ።+ ነህምያ 9:30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 አንተ ግን ለብዙ ዓመታት ታገሥካቸው፤+ በነቢያትህም አማካኝነት በመንፈስህ አስጠነቀቅካቸው፤ እነሱ ግን ለመስማት አሻፈረኝ አሉ። በመጨረሻም በምድሪቱ ለሚኖሩት ሕዝቦች አሳልፈህ ሰጠሃቸው።+ ኤርምያስ 25:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 “ከይሁዳ ንጉሥ ከአምዖን ልጅ ከኢዮስያስ 13ኛ ዓመት የግዛት ዘመን+ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ላለፉት 23 ዓመታት የይሖዋ ቃል ወደ እኔ መጣ፤ እኔም ደግሜ ደጋግሜ ነገርኳችሁ፤* እናንተ ግን አትሰሙም።+
15 የአባቶቻቸው አምላክ ይሖዋ ለሕዝቡና ለማደሪያው ስፍራ ስለራራ መልእክተኞቹን እየላከ በተደጋጋሚ ያስጠነቅቃቸው ነበር። 16 እነሱ ግን የይሖዋ ቁጣ በሕዝቡ ላይ እስኪነድና+ ፈውስ እስከማይገኝላቸው ድረስ በእውነተኛው አምላክ መልእክተኞች ላይ ያላግጡ፣+ ቃሉን ይንቁና+ በነቢያቱ ላይ ያፌዙ+ ነበር።
26 “ይሁንና ለመታዘዝ እንቢተኞች በመሆን በአንተ ላይ ዓመፁ፤+ ለሕግህም ጀርባቸውን ሰጡ።* ወደ አንተ እንዲመለሱ ሲያስጠነቅቋቸው የነበሩትን ነቢያትህን ገደሉ፤ ከፍተኛ ንቀት የሚንጸባረቅባቸውንም ተግባሮች ፈጸሙ።+
30 አንተ ግን ለብዙ ዓመታት ታገሥካቸው፤+ በነቢያትህም አማካኝነት በመንፈስህ አስጠነቀቅካቸው፤ እነሱ ግን ለመስማት አሻፈረኝ አሉ። በመጨረሻም በምድሪቱ ለሚኖሩት ሕዝቦች አሳልፈህ ሰጠሃቸው።+
3 “ከይሁዳ ንጉሥ ከአምዖን ልጅ ከኢዮስያስ 13ኛ ዓመት የግዛት ዘመን+ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ላለፉት 23 ዓመታት የይሖዋ ቃል ወደ እኔ መጣ፤ እኔም ደግሜ ደጋግሜ ነገርኳችሁ፤* እናንተ ግን አትሰሙም።+