-
ኤርምያስ 45:2-5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
2 “ባሮክ፣ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ አንተን በተመለከተ እንዲህ ይላል፦ 3 ‘አንተ “ወዮልኝ፣ ይሖዋ በሥቃዬ ላይ ሐዘን ጨምሮብኛልና! ከማሰማው ሲቃ የተነሳ ዝያለሁ፤ ማረፊያ ቦታም አላገኘሁም” ብለሃል።’
4 “እሱን እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ የገነባሁትን አፈርሳለሁ፤ የተከልኩትንም እነቅላለሁ፤ ምድሪቱን በሙሉ አወድማለሁ።+ 5 አንተ ግን ለራስህ ታላላቅ ነገሮችን ትፈልጋለህ።* እንዲህ ያሉ ነገሮችን ፈጽሞ አትፈልግ።”’*
“‘በሥጋ ለባሽ* ሁሉ ላይ ጥፋት ላመጣ ነውና’+ ይላል ይሖዋ፤ ‘በምትሄድበትም ቦታ ሁሉ ሕይወትህን* እንደ ምርኮ አድርጌ እሰጥሃለሁ።’”*+
-