የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ነገሥት 24:6
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 6 በመጨረሻም ኢዮዓቄም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤+ በእሱም ምትክ ልጁ ዮአኪን ነገሠ።

  • 2 ነገሥት 24:8
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 8 ዮአኪን+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 18 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለሦስት ወር ገዛ።+ እናቱ ነሁሽታ ትባል ነበር፤ እሷም የኢየሩሳሌም ሰው የሆነው የኤልናታን ልጅ ነበረች።

  • 2 ነገሥት 24:15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 በዚህ መንገድ ዮአኪንን+ ወደ ባቢሎን በግዞት ወሰደው፤+ በተጨማሪም የንጉሡን እናት፣ የንጉሡን ሚስቶች፣ የቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱንና በምድሪቱ ውስጥ ያሉትን ታላላቅ ሰዎች ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን በግዞት ወሰደ።

  • 2 ዜና መዋዕል 36:9, 10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 9 ዮአኪን+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 18 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለሦስት ወር ከአሥር ቀን ገዛ፤ እሱም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ።+ 10 በዓመቱ መጀመሪያ* ላይ ንጉሥ ናቡከደነጾር አገልጋዮቹን ልኮ በይሖዋ ቤት ካሉት ውድ ዕቃዎች+ ጋር ወደ ባቢሎን አመጣው።+ የአባቱን ወንድም ሴዴቅያስንም በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠው።+

  • ኤርምያስ 22:24
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 24 “‘በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ይሖዋ፣ ‘አንተ የይሁዳ ንጉሥ፣ የኢዮዓቄም+ ልጅ፣ ኮንያሁ*+ በቀኝ እጄ እንዳለ የማኅተም ቀለበት ብትሆን እንኳ ከዚያ አውጥቼ እጥልሃለሁ!

  • ኤርምያስ 22:30
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 30 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

      ‘ይህን ሰው፣ ልጅ እንደሌለውና

      በሕይወት ዘመኑ* ሁሉ ምንም እንደማይሳካለት አድርጋችሁ መዝግቡት፤

      ከዘሮቹ መካከል አንዱም እንኳ አይሳካለትምና፤

      በዳዊት ዙፋን ላይ አይቀመጥም እንዲሁም ይሁዳን ዳግመኛ አይገዛም።’”+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ