ኤርምያስ
22 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ወደ ይሁዳ ንጉሥ ቤት* ወርደህ ይህን መልእክት ተናገር። 2 እንዲህ በል፦ ‘በዳዊት ዙፋን ላይ የተቀመጥከው የይሁዳ ንጉሥ ሆይ፣ አንተም ሆንክ አገልጋዮችህ እንዲሁም በእነዚህ በሮች የሚገባው ሕዝብህ የይሖዋን ቃል ስሙ። 3 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ለፍትሕና ለጽድቅ ቁሙ። የተዘረፈውን ሰው ከአጭበርባሪው እጅ ታደጉ። ከባዕድ አገር የመጣውን ሰው አታንገላቱ፤ አባት የሌለውን ልጅ* ወይም መበለቲቱን አትበድሉ።+ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደም አታፍስሱ።+ 4 ይህን ቃል በሚገባ ብትጠብቁ፣ በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጡ ነገሥታት+ በሠረገሎችና በፈረሶች ላይ ተቀምጠው ከአገልጋዮቻቸውና ከሕዝቦቻቸው ጋር በዚህ ቤት በሮች ይገባሉ።”’+
5 “‘ይህን ቃል ባትታዘዙ ግን’ ይላል ይሖዋ፣ ‘ይህ ቤት እንደሚወድም በራሴ እምላለሁ።’+
6 “ይሖዋ የይሁዳን ንጉሥ ቤት አስመልክቶ እንዲህ ይላልና፦
‘አንተ ለእኔ እንደ ጊልያድና
እንደ ሊባኖስ ተራራ አናት ነህ።
ይሁንና ምድረ በዳ አደርግሃለሁ፤
ከተሞችህን በሙሉ ሰው አልባ አደርጋቸዋለሁ።+
ምርጥ የሆኑ አርዘ ሊባኖሶችህን ይቆርጣሉ፤
ለእሳትም ይማግዷቸዋል።+
8 “‘ብዙ ብሔራትም በዚህች ከተማ በኩል ያልፋሉ፤ እርስ በርሳቸውም “ይሖዋ በዚህች ታላቅ ከተማ ላይ ይህን ያደረገው ለምንድን ነው?” ይባባላሉ።+ 9 እነሱም እንዲህ ብለው ይመልሳሉ፦ “የአምላካቸውን የይሖዋን ቃል ኪዳን ትተው ለሌሎች አማልክት ስለሰገዱና እነሱን ስላገለገሉ ነው።”’+
10 ለሞተው ሰው አታልቅሱ፤
ደግሞም አትዘኑለት።
ይልቁንም በግዞት ለተወሰደው አምርራችሁ አልቅሱ፤
ከእንግዲህ የትውልድ አገሩን ለማየት አይመለስምና።
11 “በአባቱ በኢዮስያስ ፋንታ ስለነገሠው፣ ከዚህም ቦታ ስለሄደው ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ+ ስለ ሻሉም*+ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘ከእንግዲህ ወደዚያ አይመለስም። 12 በግዞት በተወሰደበት በዚያው ስፍራ ይሞታል እንጂ ይህን ምድር ዳግመኛ አያይም።’+
13 ጽድቅን በሚጻረር መንገድ ቤቱን ለሚገነባ፣
ፍትሕን በማዛባት ደርብ ለሚሠራ፣
የወገኑን ጉልበት እንዲሁ ለሚበዘብዝና
ደሞዙን ለማይከፍለው ወዮለት፤+
14 ‘ለራሴ ሰፊ ቤትና
የተንጣለለ ደርብ እገነባለሁ።
መስኮቶች እንዲኖረው አደርጋለሁ፤
በአርዘ ሊባኖስም እለብጠዋለሁ፤ ቀይ ቀለምም እቀባዋለሁ’ ለሚል ወዮለት!
15 በአርዘ ሊባኖስ እንጨት ከሌሎች ስለምትበልጥ በንግሥና የምትቀጥል ይመስልሃል?
16 ለተጎሳቆለው ሰውና ለድሃው ተሟግቷል፤
ስለዚህ መልካም ሆኖለት ነበር።
‘እኔን ማወቅ ማለት ይህ አይደለም?’ ይላል ይሖዋ።
17 ‘አንተ ግን ዓይንህና ልብህ ያረፈው አላግባብ በምታገኘው ጥቅም፣
ንጹሕ ደም በማፍሰስ
እንዲሁም በማጭበርበርና በቅሚያ ላይ ብቻ ነው።’
18 “ስለዚህ ይሖዋ ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮዓቄም+ እንዲህ ይላል፦
‘“ወይኔ ወንድሜን! ወይኔ እህቴን!”
ብለው አያለቅሱለትም።
“ወይኔ ጌታዬን! ክብሩ ሁሉ እንዲህ ይጥፋ!”
ብለው አያለቅሱለትም።
21 ተማምነሽ በተቀመጥሽበት ጊዜ አነጋገርኩሽ።
አንቺ ግን ‘አልታዘዝም’ አልሽ።+
ከልጅነትሽ ጀምሮ ይህን ጎዳና ተከተልሽ፤
ቃሌን አልታዘዝሽምና።+
22 ነፋስ እረኞችሽን በሙሉ ይነዳቸዋል፤+
አጥብቀው የሚወዱሽም በግዞት ይወሰዳሉ።
በዚያን ጊዜ ከሚደርስብሽ ጥፋት ሁሉ የተነሳ ታፍሪያለሽ፤ ውርደትም ትከናነቢያለሽ።
24 “‘በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ይሖዋ፣ ‘አንተ የይሁዳ ንጉሥ፣ የኢዮዓቄም+ ልጅ፣ ኮንያሁ*+ በቀኝ እጄ እንዳለ የማኅተም ቀለበት ብትሆን እንኳ ከዚያ አውጥቼ እጥልሃለሁ! 25 ሕይወትህን ለማጥፋት በሚሹ* ሰዎች እጅ፣ በምትፈራቸው ሰዎች እጅ፣ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር* እጅና በከለዳውያን እጅ አሳልፌ እሰጥሃለሁ።+ 26 አንተንና የወለደችህን እናትህን ወዳልተወለዳችሁበት፣ ወደ ሌላ አገር እወረውራችኋለሁ፤ በዚያም ትሞታላችሁ። 27 ወደሚናፍቋትም ምድር* ፈጽሞ አይመለሱም።+
28 ኮንያሁ የተባለው ይህ ሰው የተናቀና የተሰበረ ገንቦ፣
ማንም የማይፈልገው የሸክላ ዕቃ ነው?
እሱም ሆነ ዘሮቹ ወደማያውቋት ምድር የተወረወሩትና
የተጣሉት ለምንድን ነው?’+
29 ምድር፣* ምድር፣ አንቺ ምድር ሆይ፣ የይሖዋን ቃል ስሚ።
30 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦