የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ነገሥት 25:9-11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 9 እሱም የይሖዋን ቤት፣+ የንጉሡን ቤትና*+ በኢየሩሳሌም የሚገኙ ቤቶችን በሙሉ አቃጠለ፤+ የታዋቂ ሰዎችንም ቤቶች ሁሉ በእሳት አጋየ።+ 10 ከዘቦቹ አለቃ ጋር የነበረው የከለዳውያን ሠራዊት በኢየሩሳሌም ዙሪያ ያለውን ቅጥር አፈረሰ።+ 11 የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን በከተማዋ የቀሩትን በሕይወት የተረፉ ሰዎች፣ ከድተው ወደ ባቢሎን ንጉሥ የሄዱትን ሰዎችና የቀረውን ሕዝብ በግዞት ወሰደ።+

  • 2 ዜና መዋዕል 36:17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 17 ስለዚህ የከለዳውያንን+ ንጉሥ አመጣባቸው፤ እሱም ወጣቶቻቸውን በቤተ መቅደሳቸው+ ውስጥ በሰይፍ ገደለ፤+ ለወጣቱም ሆነ ለድንግሊቱ፣ ለሽማግሌውም ሆነ ለአቅመ ደካማው አልራራም።+ አምላክ ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው።+

  • 2 ዜና መዋዕል 36:19
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 19 የእውነተኛውን አምላክ ቤት አቃጠለ፤+ የኢየሩሳሌምን ቅጥር አፈረሰ፤+ የማይደፈሩ ማማዎቿን ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤ እንዲሁም ውድ የሆኑትን ዕቃዎች በሙሉ አወደመ።+

  • ነህምያ 1:3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 እነሱም እንዲህ አሉኝ፦ “ከምርኮ ተመልሰው በአውራጃው ውስጥ የሚገኙት ቀሪዎች በጣም አሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ፤ መሳለቂያም ሆነዋል።+ የኢየሩሳሌም ቅጥሮች ፈራርሰዋል፤+ በሮቿም በእሳት ተቃጥለዋል።”+

  • ኤርምያስ 52:13-15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 እሱም የይሖዋን ቤት፣ የንጉሡን ቤትና* በኢየሩሳሌም የሚገኙ ቤቶችን በሙሉ አቃጠለ፤+ ትላልቅ ቤቶችንም ሁሉ በእሳት አጋየ። 14 ከዘቦቹ አለቃ ጋር የነበረው የከለዳውያን ሠራዊት በኢየሩሳሌም ዙሪያ ያለውን ቅጥር በሙሉ አፈረሰ።+

      15 የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን ችግረኛ ከሆኑት ሰዎች መካከል የተወሰኑትንና በከተማዋ የቀሩትን በሕይወት የተረፉ ሰዎች አጋዘ። በተጨማሪም ከድተው ለባቢሎን ንጉሥ እጃቸውን የሰጡትን ሰዎችና የቀሩትን የተካኑ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ወሰደ።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ