የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ነገሥት 9:8
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 8 ይህም ቤት የፍርስራሽ ክምር ይሆናል።+ በዚያም የሚያልፉ ሰዎች ሁሉ በመገረም ትኩር ብለው እየተመለከቱ ‘ይሖዋ በዚህች ምድርና በዚህ ቤት ላይ እንዲህ ያለ ነገር ያደረገው ለምንድን ነው?’+ በማለት ያፏጫሉ።

  • 2 ዜና መዋዕል 36:17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 17 ስለዚህ የከለዳውያንን+ ንጉሥ አመጣባቸው፤ እሱም ወጣቶቻቸውን በቤተ መቅደሳቸው+ ውስጥ በሰይፍ ገደለ፤+ ለወጣቱም ሆነ ለድንግሊቱ፣ ለሽማግሌውም ሆነ ለአቅመ ደካማው አልራራም።+ አምላክ ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው።+

  • 2 ዜና መዋዕል 36:19
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 19 የእውነተኛውን አምላክ ቤት አቃጠለ፤+ የኢየሩሳሌምን ቅጥር አፈረሰ፤+ የማይደፈሩ ማማዎቿን ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤ እንዲሁም ውድ የሆኑትን ዕቃዎች በሙሉ አወደመ።+

  • መዝሙር 74:8
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  8 እነሱም ሆኑ ዘሮቻቸው በልባቸው

      “በምድሪቱ ላይ ያሉት የአምላክ መሰብሰቢያ* ቦታዎች በሙሉ ይቃጠሉ” ብለዋል።

  • መዝሙር 79:1
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 79 አምላክ ሆይ፣ ብሔራት ርስትህን+ ወረውታል፤

      ቅዱስ መቅደስህንም አርክሰዋል፤+

      ኢየሩሳሌምን የፍርስራሽ ክምር አድርገዋታል።+

  • ኤርምያስ 26:18
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 18 “የሞረሸቱ ሚክያስ+ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ+ ዘመን ትንቢት ይናገር ነበር፤ ለይሁዳም ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ብሎ ነበር፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

      “ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፤

      ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤+

      የቤቱም* ተራራ፣ በጫካ እንዳሉ ከፍ ያሉ ቦታዎች* ይሆናል።”’+

  • ሰቆቃወ ኤርምያስ 2:7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  7 ይሖዋ መሠዊያውን ናቀ፤

      መቅደሱን ተወ።+

      የማይደፈሩ ማማዎቿን ግንቦች ለጠላት አሳልፎ ሰጠ።+

      በበዓል ቀን እንደሚደረገው ሁሉ በይሖዋ ቤት በታላቅ ድምፅ ጮኹ።+

  • ሕዝቅኤል 24:21
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 21 ‘ለእስራኤል ቤት ሰዎች እንዲህ በል፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እጅግ የምትኮሩበትን፣ በፊታችሁ ተወዳጅ የሆነውንና የልባችሁ ምኞት የሆነውን* መቅደሴን ላረክስ ነው።+ ትታችኋቸው የሄዳችሁት ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ