ዘሌዋውያን 26:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 ከተሞቻችሁን ለሰይፍ አሳልፌ እሰጣለሁ፤+ መቅደሶቻችሁንም ባዶ አደርጋቸዋለሁ፤ የመሥዋዕቶቻችሁን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ አላሸትም። ኤርምያስ 26:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ይህን ቤት እንደ ሴሎ አደርገዋለሁ፤+ ይህችንም ከተማ ለምድር ብሔራት ሁሉ እርግማን አደርጋታለሁ።’”’”+ ኤርምያስ 52:12, 13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 በአምስተኛው ወር፣ ከወሩም በአሥረኛው ቀን ይኸውም ንጉሥ ናቡከደነጾር* በነገሠ በ19ኛው ዓመት፣ የዘቦች አለቃና የባቢሎን ንጉሥ አገልጋይ የሆነው ናቡዛራዳን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።+ 13 እሱም የይሖዋን ቤት፣ የንጉሡን ቤትና* በኢየሩሳሌም የሚገኙ ቤቶችን በሙሉ አቃጠለ፤+ ትላልቅ ቤቶችንም ሁሉ በእሳት አጋየ። ሕዝቅኤል 24:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ‘ለእስራኤል ቤት ሰዎች እንዲህ በል፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እጅግ የምትኮሩበትን፣ በፊታችሁ ተወዳጅ የሆነውንና የልባችሁ ምኞት የሆነውን* መቅደሴን ላረክስ ነው።+ ትታችኋቸው የሄዳችሁት ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።+ ሚክያስ 3:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ስለዚህ በእናንተ የተነሳጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፤ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤+የቤቱም* ተራራ፣ በጫካ እንዳሉ ከፍ ያሉ ቦታዎች* ይሆናል።+
12 በአምስተኛው ወር፣ ከወሩም በአሥረኛው ቀን ይኸውም ንጉሥ ናቡከደነጾር* በነገሠ በ19ኛው ዓመት፣ የዘቦች አለቃና የባቢሎን ንጉሥ አገልጋይ የሆነው ናቡዛራዳን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።+ 13 እሱም የይሖዋን ቤት፣ የንጉሡን ቤትና* በኢየሩሳሌም የሚገኙ ቤቶችን በሙሉ አቃጠለ፤+ ትላልቅ ቤቶችንም ሁሉ በእሳት አጋየ።
21 ‘ለእስራኤል ቤት ሰዎች እንዲህ በል፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እጅግ የምትኮሩበትን፣ በፊታችሁ ተወዳጅ የሆነውንና የልባችሁ ምኞት የሆነውን* መቅደሴን ላረክስ ነው።+ ትታችኋቸው የሄዳችሁት ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።+