የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ዜና መዋዕል 36:15, 16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 የአባቶቻቸው አምላክ ይሖዋ ለሕዝቡና ለማደሪያው ስፍራ ስለራራ መልእክተኞቹን እየላከ በተደጋጋሚ ያስጠነቅቃቸው ነበር። 16 እነሱ ግን የይሖዋ ቁጣ በሕዝቡ ላይ እስኪነድና+ ፈውስ እስከማይገኝላቸው ድረስ በእውነተኛው አምላክ መልእክተኞች ላይ ያላግጡ፣+ ቃሉን ይንቁና+ በነቢያቱ ላይ ያፌዙ+ ነበር።

  • ኢሳይያስ 65:2
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  2 የራሳቸውን ሐሳብ እየተከተሉ፣+

      መልካም ባልሆነ መንገድ ወደሚሄዱ+

      ግትር ሰዎች ቀኑን ሙሉ እጆቼን ዘረጋሁ፤+

  • ኤርምያስ 7:24-26
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 24 እነሱ ግን አልሰሙም ወይም ጆሯቸውን አልሰጡም፤+ ይልቁንም ግትር ሆነው ክፉ ልባቸውን በመከተል በገዛ ራሳቸው ዕቅድ* ሄዱ፤+ ወደ ፊት በመሄድ ፋንታ ወደ ኋላ ተመለሱ፤ 25 አባቶቻችሁ ከግብፅ ምድር ከወጡበት ጊዜ አንስቶ እስከዚህ ቀን ድረስ ይህን አደረጉ።+ በመሆኑም አገልጋዮቼ የሆኑትን ነቢያት ሁሉ ወደ እናንተ መላኬን ቀጠልኩ፤ ደግሜ ደጋግሜ በየዕለቱ* ላክኋቸው።+ 26 እነሱ ግን እኔን ለመስማት እንቢተኛ ሆኑ፤ ጆሯቸውንም አልሰጡም።+ ይልቁንም ግትር ሆኑ፤* አባቶቻቸው ከሠሩት የከፋ ነገር አደረጉ!

  • ኤርምያስ 35:15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 እኔም አገልጋዮቼን ነቢያትን ሁሉ ወደ እናንተ መላኬን ቀጠልኩ፤ እንዲህ በማለትም ደግሜ ደጋግሜ* ላክኋቸው፦+ ‘እባካችሁ፣ እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤+ ትክክል የሆነውንም ነገር አድርጉ! ሌሎችን አማልክት አትከተሉ፤ ደግሞም አታገልግሏቸው። እንዲህ ካደረጋችሁ ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጠኋት ምድር ትኖራላችሁ።’+ እናንተ ግን ጆሯችሁን አልሰጣችሁም፤ እኔንም አልሰማችሁም።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ