10 “አንተም አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፣ አትፍራ” ይላል ይሖዋ፤
“እስራኤል ሆይ፣ አትሸበር።+
አንተን ከሩቅ አገር፣
ዘርህንም ተማርኮ ከተወሰደበት ምድር እታደጋለሁና።+
ያዕቆብ ይመለሳል፤ ሳይረበሽም ተረጋግቶ ይቀመጣል፤
የሚያስፈራቸው አይኖርም።”+
11 “እኔ አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋር ነኝና” ይላል ይሖዋ።
“አንተን የበተንኩባቸውን ብሔራት ሁሉ ግን ፈጽሞ አጠፋቸዋለሁ፤+
ይሁን እንጂ አንተን ሙሉ በሙሉ አላጠፋህም።+
በተገቢው መጠን እገሥጽሃለሁ እንጂ
በምንም ዓይነት ሳልቀጣ አልተውህም።”+