27 ‘አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፣ አትፍራ፤
እስራኤልም ሆይ፣ አትሸበር።+
አንተን ከሩቅ ቦታ፣
ዘሮችህንም ተማርከው ከተወሰዱበት ምድር አድናለሁና።+
ያዕቆብ ይመለሳል፤ የሚያስፈራውም ሳይኖር
ተረጋግቶና ሰላም አግኝቶ ይቀመጣል።+
28 ስለዚህ አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፣ አትፍራ’ ይላል ይሖዋ፤
‘እኔ ከአንተ ጋር ነኝና።
አንተን የበተንኩባቸውን ብሔራት ሁሉ ፈጽሞ አጠፋቸዋለሁ፤+
አንተን ግን ሙሉ በሙሉ አላጠፋህም።+
በተገቢው መጠን እገሥጽሃለሁ እንጂ+
በምንም ዓይነት ሳልቀጣ አልተውህም።’”