የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 46
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • በግብፅ ላይ የተነገረ ትንቢት (1-26)

        • ናቡከደነጾር ግብፅን ድል ያደርጋል (13, 26)

      • ለእስራኤል የተገባ ቃል (27, 28)

ኤርምያስ 46:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 1:10

ኤርምያስ 46:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 23:36፤ ኤር 25:1፤ 36:1
  • +2ዜና 35:20
  • +ኤር 25:15, 19፤ ሕዝ 29:2፤ 32:2

ኤርምያስ 46:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    አብዛኛውን ጊዜ ቀስተኞች የሚይዙት ትንሽ ጋሻ።

ኤርምያስ 46:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 24:7

ኤርምያስ 46:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 29:3፤ 32:2

ኤርምያስ 46:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የኩሽ።”

  • *

    ቃል በቃል “የመርገጥና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 27:2, 10
  • +ኢሳ 66:19
  • +ዘፍ 10:6, 13፤ ሕዝ 30:4, 5

ኤርምያስ 46:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እርድ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 24:7

ኤርምያስ 46:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 37:25፤ ኤር 8:22
  • +ሕዝ 30:21

ኤርምያስ 46:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 32:9

ኤርምያስ 46:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 43:10፤ ሕዝ 29:19፤ 30:10

ኤርምያስ 46:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በሜምፊስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 44:1፤ ሕዝ 29:10፤ 30:6
  • +ኤር 43:4, 7፤ ሕዝ 30:18

ኤርምያስ 46:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የተወሰነውን ጊዜ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 29:3

ኤርምያስ 46:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ግብፅን ድል የሚያደርገውን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 19:17, 22፤ መሳ 4:6፤ መዝ 89:12
  • +1ነገ 18:42

ኤርምያስ 46:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሜምፊስ።”

  • *

    “ጠፍ መሬት ትሆናለች” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 32:15

ኤርምያስ 46:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 46:5, 15

ኤርምያስ 46:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እንጨት እንደሚሰበስቡ።”

ኤርምያስ 46:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 30:10

ኤርምያስ 46:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቴብስን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 30:14
  • +ናሆም 3:8
  • +ዘፀ 12:12፤ ኢሳ 19:1፤ ኤር 43:12, 13
  • +ኤር 17:5፤ 42:14

ኤርምያስ 46:26

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሳቸውን ለሚሹ።”

  • *

    ቃል በቃል “ለናቡከደረጾርና።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 43:10, 11፤ ሕዝ 32:11
  • +ሕዝ 29:13, 14

ኤርምያስ 46:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 41:13፤ 43:1, 2፤ 44:2
  • +ኢሳ 11:11፤ ኤር 50:19፤ ሕዝ 39:27፤ አሞጽ 9:14፤ ሶፎ 3:20
  • +ኤር 23:3, 6፤ 30:10, 11

ኤርምያስ 46:28

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አርምሃለሁ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 25:9
  • +ኤር 5:10፤ አሞጽ 9:8
  • +ኤር 10:24

ተዛማጅ ሐሳብ

ኤር. 46:1ኤር 1:10
ኤር. 46:22ነገ 23:36፤ ኤር 25:1፤ 36:1
ኤር. 46:22ዜና 35:20
ኤር. 46:2ኤር 25:15, 19፤ ሕዝ 29:2፤ 32:2
ኤር. 46:62ነገ 24:7
ኤር. 46:8ሕዝ 29:3፤ 32:2
ኤር. 46:9ሕዝ 27:2, 10
ኤር. 46:9ኢሳ 66:19
ኤር. 46:9ዘፍ 10:6, 13፤ ሕዝ 30:4, 5
ኤር. 46:102ነገ 24:7
ኤር. 46:11ዘፍ 37:25፤ ኤር 8:22
ኤር. 46:11ሕዝ 30:21
ኤር. 46:12ሕዝ 32:9
ኤር. 46:13ኤር 43:10፤ ሕዝ 29:19፤ 30:10
ኤር. 46:14ኤር 44:1፤ ሕዝ 29:10፤ 30:6
ኤር. 46:14ኤር 43:4, 7፤ ሕዝ 30:18
ኤር. 46:17ሕዝ 29:3
ኤር. 46:18ኢያሱ 19:17, 22፤ መሳ 4:6፤ መዝ 89:12
ኤር. 46:181ነገ 18:42
ኤር. 46:19ሕዝ 32:15
ኤር. 46:21ኤር 46:5, 15
ኤር. 46:24ሕዝ 30:10
ኤር. 46:25ሕዝ 30:14
ኤር. 46:25ናሆም 3:8
ኤር. 46:25ዘፀ 12:12፤ ኢሳ 19:1፤ ኤር 43:12, 13
ኤር. 46:25ኤር 17:5፤ 42:14
ኤር. 46:26ኤር 43:10, 11፤ ሕዝ 32:11
ኤር. 46:26ሕዝ 29:13, 14
ኤር. 46:27ኢሳ 41:13፤ 43:1, 2፤ 44:2
ኤር. 46:27ኢሳ 11:11፤ ኤር 50:19፤ ሕዝ 39:27፤ አሞጽ 9:14፤ ሶፎ 3:20
ኤር. 46:27ኤር 23:3, 6፤ 30:10, 11
ኤር. 46:28ኤር 25:9
ኤር. 46:28ኤር 5:10፤ አሞጽ 9:8
ኤር. 46:28ኤር 10:24
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኤርምያስ 46:1-28

ኤርምያስ

46 ብሔራትን አስመልክቶ ወደ ነቢዩ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦+ 2 የኢዮስያስ ልጅ የሆነው የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም+ በነገሠ በአራተኛው ዓመት በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ የነበረውንና የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* በካርከሚሽ ድል ያደረገውን የግብፅን ንጉሥ የፈርዖን ኒካዑን+ ሠራዊት በተመለከተ ለግብፅ+ የተነገረ መልእክት፦

 3 “ትንሹንና* ትልቁን ጋሻችሁን አዘጋጁ፤

ለውጊያም ውጡ።

 4 እናንተ ፈረሰኞች፣ ፈረሶችን ጫኑ፤ በላያቸውም ተቀመጡ።

ቦታ ቦታችሁን ያዙ፤ የራስ ቁራችሁንም አድርጉ።

ጦሩን ወልውሉ፤ ጥሩራችሁንም ልበሱ።

 5 ‘እንዲህ ተሸብረው ያየኋቸው ለምንድን ነው?

እያፈገፈጉ ነው፤ ተዋጊዎቻቸው ተፍረክርከዋል።

በድንጋጤ እግሬ አውጪኝ ብለዋል፤ ተዋጊዎቻቸው ወደ ኋላ አልተመለከቱም።

በየቦታው ሽብር ነግሦአል’ ይላል ይሖዋ።

 6 ‘ፈጣን የሆኑት መሸሽ አይችሉም፤ ተዋጊዎቹም ማምለጥ አይችሉም።

በሰሜን በኤፍራጥስ ወንዝ ዳርቻ

ተሰናክለው ወድቀዋል።’+

 7 እንደ አባይ ወንዝ፣

እንደሚናወጥም የወንዝ ውኃ ሆኖ የሚመጣው ይህ ማን ነው?

 8 ግብፅ እንደ አባይ ወንዝና+

እንደሚናወጥ የወንዝ ውኃ ሆኖ ይመጣል፤

ደግሞም ‘እወጣለሁ፤ ምድርንም እሸፍናለሁ።

ከተማዋንና ነዋሪዎቿን አጠፋለሁ’ ይላል።

 9 እናንተ ፈረሶች፣ ወደ ላይ ውጡ!

እናንተ ሠረገሎች፣ በፍጥነት ገስግሱ!

ተዋጊዎቹ ይውጡ፤

ጋሻ የሚያነግቡት የኢትዮጵያ* እና የፑጥ ሰዎች+

እንዲሁም ደጋን የመወጠርና*+ በጥበብ የመጠቀም ችሎታ ያላቸው የሉድ+ ሰዎች ይውጡ።

10 “ያ ቀን የሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ነው፤ ጠላቶቹን የሚበቀልበት የበቀል ቀን ነው። ሰይፉ ይበላል፤ ይጠግባልም፤ ደማቸውንም እስኪረካ ድረስ ይጠጣል፤ ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ በኤፍራጥስ ወንዝ+ አጠገብ በሚገኘው የሰሜን ምድር መሥዋዕት* አዘጋጅቷልና።

11 ድንግሊቱ የግብፅ ሴት ልጅ ሆይ፣

ወደ ጊልያድ ወጥተሽ በለሳን አምጪ።+

መድኃኒት የምታበዢው እንዲያው በከንቱ ነው፤

ፈውስ አታገኚምና።+

12 ብሔራት በአንቺ ላይ የደረሰውን ውርደት ሰምተዋል፤+

ጩኸትሽም አገር ምድሩን አናውጧል።

ተዋጊ በተዋጊው ይሰናከላልና፤

ሁለቱም በአንድነት ተያይዘው ወድቀዋል።”

13 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* የግብፅን ምድር ለመምታት ስለመምጣቱ ይሖዋ ለነቢዩ ኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦+

14 “ይህን በግብፅ ተናገሩ፤ በሚግዶል+ አውጁት።

በኖፍ* እና በጣፍነስ+ አውጁት።

እንዲህም በሉ፦ ‘ቦታ ቦታችሁን ያዙ፤ ተዘጋጁም፤

ሰይፍ በዙሪያችሁ ያለውን ሁሉ ይበላልና።

15 ኃያላኖቻችሁ ተጠራርገው የጠፉት ለምንድን ነው?

ጸንተው መቆም አልቻሉም፤

ይሖዋ ገፍትሮ ጥሏቸዋልና።

16 ብዙዎቹ ይሰናከላሉ፤ ደግሞም ይወድቃሉ።

እርስ በርሳቸውም “ተነሱ!

ከጨካኙ ሰይፍ የተነሳ

ወደ ሕዝባችንና ወደ ትውልድ አገራችን እንመለስ” ይባባላሉ።’

17 በዚያም ‘ያገኘውን አጋጣሚ* ያልተጠቀመበት

የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን

ጉራውን የሚነዛው በከንቱ ነው’ ብለዋል።+

18 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ተብሎ የተጠራው ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ‘በሕያውነቴ እምላለሁ፤

እሱ* በተራሮች መካከል እንዳለው እንደ ታቦርና+

በባሕር አጠገብ እንዳለው እንደ ቀርሜሎስ+ ሆኖ ይመጣል።

19 አንቺ በግብፅ የምትኖሪ ሴት ልጅ ሆይ፣

በግዞት ለመሄድ ጓዝሽን አሰናጂ።

ኖፍ* አስፈሪ ቦታ ትሆናለችና፤

በእሳት ትጋያለች፤* ማንም ሰው የማይኖርባትም ምድር ትሆናለች።+

20 ግብፅ እንደምታምር ጊደር ናት፤

ሆኖም ከሰሜን ተናዳፊ ዝንቦች ይመጡባታል።

21 በመካከሏ ያሉት ቅጥረኛ ወታደሮችም እንኳ እንደሰቡ ጥጆች ናቸው፤

ይሁንና እነሱም ጭምር ወደ ኋላ ተመልሰው በአንድነት ሸሽተዋል።

ጸንተው መቆም አልቻሉም፤+

የሚጠፉበት ቀን፣

የሚመረመሩበትም ጊዜ ደርሶባቸዋልና።’

22 ‘ድምፅዋ እየተጥመዘመዘ እንደሚሄድ እባብ ድምፅ ነው፤

ዛፍ እንደሚቆርጡ* ሰዎች

መጥረቢያ ይዘው በኃይል ይመጡባታልና።

23 በውስጡ ማለፍ የማይቻል ቢመስልም ጫካዋን ይመነጥራሉ’ ይላል ይሖዋ።

‘ቁጥራቸው ከአንበጣ ይበልጥ ይበዛልና፤ ስፍር ቁጥርም የላቸውም።

24 የግብፅ ሴት ልጅ ለኀፍረት ትዳረጋለች።

ለሰሜን ሰዎች ትሰጣለች።’+

25 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አሁን ትኩረቴን በኖእ*+ ከተማ ወደሚገኘው ወደ አምዖን፣+ ወደ ፈርዖን፣ ወደ ግብፅ፣ ወደ አማልክቷና+ ወደ ነገሥታቷ፣ አዎ በፈርዖንና በእሱ ወደሚታመኑት ሰዎች ሁሉ አደርጋለሁ።’+

26 “‘ሕይወታቸውን ማጥፋት ለሚሹ* ሰዎች፣ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾርና* ለአገልጋዮቹ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።+ ከዚያ በኋላ ግን እንደቀድሞው ዘመን የሰው መኖሪያ ትሆናለች’ ይላል ይሖዋ።+

27 ‘አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፣ አትፍራ፤

እስራኤልም ሆይ፣ አትሸበር።+

አንተን ከሩቅ ቦታ፣

ዘሮችህንም ተማርከው ከተወሰዱበት ምድር አድናለሁና።+

ያዕቆብ ይመለሳል፤ የሚያስፈራውም ሳይኖር

ተረጋግቶና ሰላም አግኝቶ ይቀመጣል።+

28 ስለዚህ አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፣ አትፍራ’ ይላል ይሖዋ፤

‘እኔ ከአንተ ጋር ነኝና።

አንተን የበተንኩባቸውን ብሔራት ሁሉ ፈጽሞ አጠፋቸዋለሁ፤+

አንተን ግን ሙሉ በሙሉ አላጠፋህም።+

በተገቢው መጠን እገሥጽሃለሁ* እንጂ+

በምንም ዓይነት ሳልቀጣ አልተውህም።’”

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ