ኤርምያስ
47 ፈርዖን ጋዛን ከመውጋቱ በፊት ፍልስጤማውያንን+ በተመለከተ ወደ ነቢዩ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው። 2 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“እነሆ፣ ከሰሜን ውኃ እየመጣ ነው።
የሚያጥለቀልቅም ወንዝ ይሆናል።
ምድሪቱንና በውስጧ ያሉትን ሁሉ፣
ከተማዋንና ነዋሪዎቿን ያጥለቀልቃል።
ሰዎቹ ይጮኻሉ፤
በምድሪቱም የሚኖሩ ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ።
3 ከድንጉላ ፈረሶቹ ኃይለኛ የኮቴ ድምፅ፣
ከሚንገጫገጩት የጦር ሠረገሎቹ ድምፅና
ከመንኮራኩሮቹ* የማያባራ ድምፅ የተነሳ
አባቶች እጃቸው ስለሚዝል
ልጆቻቸውን ለመርዳት እንኳ ወደ ኋላ አይዞሩም፤
4 ምክንያቱም የሚመጣው ቀን ፍልስጤማውያንን+ ሁሉ ያጠፋል፤
5 ጋዛ ትመለጣለች።*
አስቀሎን ጸጥ ትላለች።+
6 አንተ የይሖዋ ሰይፍ!+
የማታርፈው እስከ መቼ ነው?
ወደ ሰገባህ ግባ።
እረፍ፤ ጸጥ ብለህም ተቀመጥ።
7 ይሖዋ ትእዛዝ ሰጥቶት እያለ
እንዴት አርፎ ሊቀመጥ ይችላል?
ትእዛዝ የተሰጠው በአስቀሎንና በባሕሩ ዳርቻ ላይ ነው፤+
በዚያ መድቦታል።”