4 ሃሽቦንና ኤልዓሌ+ ያለቅሳሉ፤
ድምፃቸው እስከ ያሃጽ+ ድረስ ተሰምቷል።
ከዚህም የተነሳ የሞዓብ ተዋጊዎች ይጮኻሉ።
እሱም ይንቀጠቀጣል።
5 ልቤ ስለ ሞዓብ ያለቅሳል።
የሚሸሹት የሞዓብ ሰዎች እስከ ዞአርና+ እስከ ኤግላት ሸሊሺያ+ ድረስ ተሰደዱ።
እያለቀሱ የሉሂትን ዳገት ይወጣሉ፤
በደረሰባቸው ድንገተኛ ጥፋት የተነሳ ወደ ሆሮናይም በሚወስደው መንገድ ላይ ሲሄዱ ይጮኻሉ።+
6 የኒምሪም ውኃዎች ደርቀዋልና፤
ለምለሙ የግጦሽ መስክ ደርቋል፤
ሣሩ ጠፍቷል፤ አንድም የለመለመ ነገር አይታይም።