7 አንድን ብሔር ወይም አንድን መንግሥት እንደምነቅል፣ እንደማፈርስና እንደማጠፋ በተናገርኩ ጊዜ፣+ 8 ያ ብሔር እኔ ያወገዝኩትን ክፉ ነገር ቢተው፣ ሐሳቤን ለውጬ በእሱ ላይ ላመጣው ያሰብኩትን ጥፋት እተወዋለሁ።+ 9 ሆኖም አንድን ብሔር ወይም አንድን መንግሥት እንደምገነባውና እንደምተክለው በተናገርኩ ጊዜ፣ 10 በፊቴ ክፉ የሆነውን ነገር ቢያደርግና ድምፄን ባይሰማ እኔም ሐሳቤን ለውጬ ለእሱ አደርገዋለሁ ብዬ ያሰብኩትን መልካም ነገር እተወዋለሁ።’