የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘሌዋውያን 26:32
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 32 እኔ ራሴ ምድሪቱን ባድማ አደርጋታለሁ፤+ በዚያ የሚኖሩ ጠላቶቻችሁም በመደነቅ ይመለከቷታል።+

  • 2 ዜና መዋዕል 36:20, 21
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 20 ከሰይፍ የተረፉትንም ሁሉ ማርኮ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፤+ እነሱም የፋርስ መንግሥት* መግዛት እስከጀመረበት ጊዜ ድረስ+ የእሱና የወንዶች ልጆቹ አገልጋዮች ሆኑ፤+ 21 ይህም የሆነው ይሖዋ በኤርምያስ በኩል የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ፣+ ምድሪቱ የሰንበት ዕዳዋን እስክትከፍል ድረስ ነው።+ ፈራርሳ በቆየችባቸው ጊዜያት ሁሉ፣ 70 ዓመት እስኪፈጸም ድረስ ሰንበትን አከበረች።+

  • ኢሳይያስ 6:11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 በዚህ ጊዜ “ይሖዋ ሆይ፣ እስከ መቼ ነው?” አልኩ። እሱም እንዲህ አለኝ፦

      “ከተሞች እስኪፈራርሱና የሚኖርባቸው እስኪያጡ፣

      ቤቶችም ሰው አልባ እስኪሆኑ፣

      ምድሪቱም እስክትጠፋና ባድማ እስክትሆን ድረስ ነው፤+

  • ኤርምያስ 10:22
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 22 አዳምጡ! አንድ ወሬ ስሙ! ወደዚህ እየመጣ ነው!

      የይሁዳን ከተሞች ባድማና የቀበሮዎች ጎሬ ሊያደርግ+

      ከሰሜን ምድር ድም፣ ድም የሚል ኃይለኛ ድምፅ እየቀረበ ነው።+

  • ሕዝቅኤል 33:28
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 28 ምድሪቱን ፈጽሞ ባድማ አደርጋታለሁ፤+ ከልክ ያለፈ ኩራቷም ይጠፋል፤ የእስራኤልም ተራሮች ባድማ ይሆናሉ፤+ የሚያልፍባቸውም አይኖርም።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ