-
ዘዳግም 29:22-24አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
22 “መጪው የልጆቻችሁ ትውልድና ከሩቅ ምድር የሚመጡት የባዕድ አገር ሰዎች በምድሪቱ ላይ የወረዱትን መቅሰፍቶች ይኸውም ይሖዋ በላይዋ ላይ ያመጣውን በሽታ 23 እንዲሁም ይሖዋ በቁጣውና በመዓቱ ሰዶምንና ገሞራን፣+ አድማህንና ጸቦይምን+ እንደገለባበጠ ሁሉ መላዋ ምድር እንዳይዘራባት፣ እንዳታቆጠቁጥ ወይም ምንም ዓይነት ተክል እንዳታበቅል የላከውን ድኝ፣ ጨውና እሳት ሲመለከቱ 24 እነሱም ሆኑ ሁሉም ብሔራት ‘ይሖዋ በዚህች ምድር ላይ እንዲህ ያደረገው ለምንድን ነው?+ ይህን ታላቅ ቁጣስ ምን አመጣው?’ ይላሉ።
-
-
ኤርምያስ 18:16አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
በዚያ የሚያልፍ ሁሉ በፍርሃት አፍጥጦ ይመለከታል፤ ራሱንም ይነቀንቃል።+
-
-
ሕዝቅኤል 5:15አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
15 በቁጣ፣ በንዴትና በኃይለኛ ቅጣት የፍርድ እርምጃ ስወስድብሽ በዙሪያሽ ባሉ ብሔራት ዘንድ መሳለቂያና መዘባበቻ+ ደግሞም የማስጠንቀቂያ ምሳሌና ማስፈራሪያ ትሆኛለሽ። እኔ ይሖዋ ይህን ተናግሬአለሁ።
-