22 “ስለዚህ ኦሆሊባ ሆይ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ተጸይፈሽ የራቅሻቸውን ፍቅረኞችሽን በአንቺ ላይ አስነሳለሁ፤+ እነሱንም ከየአቅጣጫው አመጣብሻለሁ፤+ 23 እነሱም የባቢሎን ልጆችና+ ከለዳውያን+ ሁሉ እንዲሁም የአሦርን ልጆች ሁሉ ጨምሮ የጰቆድ፣+ የሾአ እና የቆአ ሰዎች ናቸው። ሁሉም መልከ ቀና ወጣቶች፣ ገዢዎችና የበታች ገዢዎች፣ ተዋጊዎችና የተመረጡ አማካሪዎች እንዲሁም ፈረሰኞች ናቸው።