-
ኤርምያስ 49:19-21አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
19 “እነሆ፣ አንድ ሰው፣ እንደ አንበሳ በዮርዳኖስ ዳርቻ ከሚገኙ ጥቅጥቅ ያሉ ጥሻዎች ወጥቶ+ አስተማማኝ በሆነው መሰማሪያ ላይ ይመጣል፤ እኔ ግን ወዲያውኑ ከእሷ አባርረዋለሁ። የተመረጠውን በእሷ ላይ እሾማለሁ። እንደ እኔ ያለ ማነው? ማንስ ሊሟገተኝ ይችላል? በእኔ ፊት ሊቆም የሚችል እረኛ የትኛው ነው?+ 20 ስለዚህ እናንተ ሰዎች፣ ይሖዋ በኤዶም ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔና* በቴማን+ ነዋሪዎች ላይ ያሰበውን ሐሳብ ስሙ፦
ከመንጋው መካከል ትናንሽ የሆኑት ተጎትተው መወሰዳቸው አይቀርም።
ከእነሱ የተነሳ መሰማሪያቸውን ባድማ ያደርጋል።+
21 እነሱ ሲወድቁ ከሚሰማው ታላቅ ድምፅ የተነሳ ምድር ተናወጠች።
ጩኸት ይሰማል!
ድምፁም እስከ ቀይ ባሕር+ ድረስ አስተጋብቷል።
-