-
ኤርምያስ 50:44-46አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
44 “እነሆ፣ አንድ ሰው፣ እንደ አንበሳ በዮርዳኖስ ዳርቻ ከሚገኙ ጥቅጥቅ ያሉ ጥሻዎች ወጥቶ አስተማማኝ በሆነው መሰማሪያ ላይ ይመጣል፤ እኔ ግን ወዲያውኑ ከእሷ አባርራቸዋለሁ። የተመረጠውን በእሷ ላይ እሾማለሁ።+ እንደ እኔ ያለ ማነው? ማንስ ሊሟገተኝ ይችላል? በእኔ ፊት ሊቆም የሚችል እረኛ የትኛው ነው?+ 45 ስለዚህ እናንተ ሰዎች፣ ይሖዋ በባቢሎን ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔና*+ በከለዳውያን ምድር ላይ ያሰበውን ሐሳብ ስሙ።
ከመንጋው መካከል ትናንሽ የሆኑት ተጎትተው መወሰዳቸው አይቀርም።
ከእነሱ የተነሳ መሰማሪያቸውን ባድማ ያደርጋል።+
46 ባቢሎን ስትያዝ ከሚሰማው ድምፅ የተነሳ ምድር ትናወጣለች፤
ከብሔራትም መካከል ጩኸት ይሰማል።”+
-