-
ዘዳግም 28:53-57አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
53 ከሚያስጨንቀው ከበባና ጠላትህ በአንተ ላይ ከሚያደርሰው ሥቃይ የተነሳ አምላክህ ይሖዋ የሰጠህን የሆድህን ፍሬ ይኸውም የወንዶችና የሴቶች ልጆችህን ሥጋ ትበላለህ።+
54 “ሌላው ቀርቶ በመካከልህ ያለ በምቾትና በቅምጥልነት ይኖር የነበረ ሰው እንኳ በወንድሙ፣ በሚወዳት ሚስቱ ወይም በተረፉት ልጆቹ ላይ ይጨክናል፤ 55 ከሚበላው የልጆቹ ሥጋ ላይ ምንም ነገር አያካፍላቸውም፤ ምክንያቱም ከሚያስጨንቀው ከበባና ጠላትህ በከተሞችህ ላይ ከሚያመጣው ሥቃይ የተነሳ የሚተርፈው ምንም ነገር አይኖረውም።+ 56 ከቅምጥልነቷ የተነሳ መሬት ለመርገጥ እንኳ ትጸየፍ የነበረች+ በመካከልህ ያለች ቅምጥልና በምቾት የምትኖር ሴትም በምትወደው ባሏ፣ በወንድ ልጇ ወይም በሴት ልጇ ላይ ትጨክናለች፤ 57 ሌላው ቀርቶ ከወሊድ በኋላ ከእግሮቿ መካከል በሚወጣው ነገር ሁሉና በምትወልዳቸው ልጆች ላይ ትጨክናለች፤ ምክንያቱም ከሚያስጨንቀው ከበባና ጠላትህ በከተሞችህ ላይ ከሚያመጣው ሥቃይ የተነሳ በድብቅ ትበላቸዋለች።
-
-
2 ነገሥት 25:3-7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 በአራተኛው ወር፣ ዘጠነኛ ቀን በከተማዋ ውስጥ ረሃቡ እጅግ ከፋ፤+ በምድሪቱ የሚኖሩትም ሰዎች የሚላስ የሚቀመስ አጡ።+ 4 የከተማዋ ቅጥር ተደረመሰ፤+ ከለዳውያን ከተማዋን ከበው ሳለም ወታደሮቹ ሁሉ በንጉሡ የአትክልት ቦታ አቅራቢያ ባለው መንገድ፣ በሁለቱ ቅጥሮች መካከል በሚገኘው በር በኩል በሌሊት ወጥተው ሸሹ፤ ንጉሡም ወደ አረባ በሚወስደው መንገድ ሄደ።+ 5 ይሁንና የከለዳውያን ሠራዊት ንጉሡን አሳደደ፤ እሱንም በኢያሪኮ በረሃማ ሜዳ ላይ ደረሱበት፤ ወታደሮቹም ሁሉ ጥለውት ተበታተኑ። 6 ከዚያም ንጉሡን ይዘው+ በሪብላ ወደነበረው የባቢሎን ንጉሥ አመጡት፤ ደግሞም ፈረዱበት። 7 የሴዴቅያስን ወንዶች ልጆች ዓይኑ እያየ አረዷቸው፤ ከዚያም ናቡከደነጾር የሴዴቅያስን ዓይን አሳወረ፤ በመዳብ የእግር ብረት አስሮም ወደ ባቢሎን ወሰደው።+
-