ኤርምያስ 24:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 “‘ይሁንና ከመጥፎነታቸው የተነሳ ሊበሉ የማይችሉትን መጥፎ በለሶች+ በተመለከተ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን፣+ መኳንንቱን፣ በዚህች ምድር ላይ የሚቀሩትን የኢየሩሳሌም ቀሪዎችና በግብፅ ምድር የሚኖሩትን በዚሁ ዓይን እመለከታቸዋለሁ።+ ኤርምያስ 34:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስንና መኳንንቱን ሁሉ ለጠላቶቻቸው፣ ሕይወታቸውን ማጥፋት ለሚሹ* ሰዎችና እናንተን መውጋት ትቶ ለተመለሰው+ የባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት አሳልፌ እሰጣለሁ።’+ ኤርምያስ 37:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ከዚያም ንጉሥ ሴዴቅያስ ልኮ አስመጣው፤ ንጉሡም በቤቱ* ውስጥ በሚስጥር ጠየቀው።+ “ከይሖዋ የመጣ ቃል አለ?” አለው። ኤርምያስም “አዎ፣ አለ!” ሲል መለሰለት፤ አክሎም “በባቢሎን ንጉሥ እጅ አልፈህ ትሰጣለህ!” አለው።+ ኤርምያስ 38:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ለባቢሎን ንጉሥ መኳንንት እጅህን የማትሰጥ ከሆነ* ግን ይህች ከተማ ለከለዳውያን አልፋ ትሰጣለች፤ እነሱም በእሳት ያቃጥሏታል፤+ አንተም ከእጃቸው አታመልጥም።’”+
8 “‘ይሁንና ከመጥፎነታቸው የተነሳ ሊበሉ የማይችሉትን መጥፎ በለሶች+ በተመለከተ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን፣+ መኳንንቱን፣ በዚህች ምድር ላይ የሚቀሩትን የኢየሩሳሌም ቀሪዎችና በግብፅ ምድር የሚኖሩትን በዚሁ ዓይን እመለከታቸዋለሁ።+
21 የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስንና መኳንንቱን ሁሉ ለጠላቶቻቸው፣ ሕይወታቸውን ማጥፋት ለሚሹ* ሰዎችና እናንተን መውጋት ትቶ ለተመለሰው+ የባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት አሳልፌ እሰጣለሁ።’+
17 ከዚያም ንጉሥ ሴዴቅያስ ልኮ አስመጣው፤ ንጉሡም በቤቱ* ውስጥ በሚስጥር ጠየቀው።+ “ከይሖዋ የመጣ ቃል አለ?” አለው። ኤርምያስም “አዎ፣ አለ!” ሲል መለሰለት፤ አክሎም “በባቢሎን ንጉሥ እጅ አልፈህ ትሰጣለህ!” አለው።+
18 ለባቢሎን ንጉሥ መኳንንት እጅህን የማትሰጥ ከሆነ* ግን ይህች ከተማ ለከለዳውያን አልፋ ትሰጣለች፤ እነሱም በእሳት ያቃጥሏታል፤+ አንተም ከእጃቸው አታመልጥም።’”+