የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 34
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ለሴዴቅያስ የተነገረ የፍርድ መልእክት (1-7)

      • ለባሪያዎች ነፃነት አስገኝቶ የነበረው ቃል ኪዳን ፈረሰ (8-22)

ኤርምያስ 34:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 25:1፤ ኤር 32:2፤ 39:1፤ 52:4

ኤርምያስ 34:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 36:11፤ ኤር 37:1
  • +ኤር 21:10፤ 32:28, 29፤ 39:8

ኤርምያስ 34:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 37:17፤ 39:5
  • +2ነገ 25:6, 7፤ ሕዝ 12:13

ኤርምያስ 34:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 17:16

ኤርምያስ 34:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሚክ 1:13
  • +ኢያሱ 15:20, 35
  • +ኤር 4:5

ኤርምያስ 34:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 21:2

ኤርምያስ 34:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 13:3
  • +ዘፀ 24:7

ኤርምያስ 34:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 21:2፤ ዘሌ 25:10, 39-42፤ ዘዳ 15:12

ኤርምያስ 34:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ዛሬ።”

ኤርምያስ 34:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እንደ ነፍሳቸው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 19:12

ኤርምያስ 34:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በበሽታና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 21:2፤ ዘሌ 25:10
  • +2ነገ 25:3፤ ኤር 21:7
  • +ኤር 15:2, 4፤ 29:18

ኤርምያስ 34:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 15:10, 17

ኤርምያስ 34:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሳቸውን ለሚሹ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:26፤ መዝ 79:2፤ ኤር 16:4

ኤርምያስ 34:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሳቸውን ለሚሹ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 37:5
  • +2ነገ 25:6, 7፤ ሰቆ 4:20

ኤርምያስ 34:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 25:9, 10፤ ኤር 32:29፤ 39:8
  • +ዘሌ 26:33፤ ኤር 44:2

ተዛማጅ ሐሳብ

ኤር. 34:12ነገ 25:1፤ ኤር 32:2፤ 39:1፤ 52:4
ኤር. 34:22ዜና 36:11፤ ኤር 37:1
ኤር. 34:2ኤር 21:10፤ 32:28, 29፤ 39:8
ኤር. 34:3ኤር 37:17፤ 39:5
ኤር. 34:32ነገ 25:6, 7፤ ሕዝ 12:13
ኤር. 34:5ሕዝ 17:16
ኤር. 34:7ሚክ 1:13
ኤር. 34:7ኢያሱ 15:20, 35
ኤር. 34:7ኤር 4:5
ኤር. 34:8ዘፀ 21:2
ኤር. 34:13ዘፀ 13:3
ኤር. 34:13ዘፀ 24:7
ኤር. 34:14ዘፀ 21:2፤ ዘሌ 25:10, 39-42፤ ዘዳ 15:12
ኤር. 34:16ዘሌ 19:12
ኤር. 34:17ዘፀ 21:2፤ ዘሌ 25:10
ኤር. 34:172ነገ 25:3፤ ኤር 21:7
ኤር. 34:17ኤር 15:2, 4፤ 29:18
ኤር. 34:18ዘፍ 15:10, 17
ኤር. 34:20ዘዳ 28:26፤ መዝ 79:2፤ ኤር 16:4
ኤር. 34:21ኤር 37:5
ኤር. 34:212ነገ 25:6, 7፤ ሰቆ 4:20
ኤር. 34:222ነገ 25:9, 10፤ ኤር 32:29፤ 39:8
ኤር. 34:22ዘሌ 26:33፤ ኤር 44:2
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኤርምያስ 34:1-22

ኤርምያስ

34 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር፣* ሠራዊቱ ሁሉ፣ በእሱ ግዛት ሥር ያሉ የምድር መንግሥታት ሁሉ እንዲሁም ሕዝቡ ሁሉ ኢየሩሳሌምንና በዙሪያዋ ያሉትን ከተሞች በሙሉ እየወጉ ሳሉ ወደ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦+

2 “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሂድና የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን+ አናግረው፤ እንዲህም በለው፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ይህችን ከተማ ለባቢሎን ንጉሥ አሳልፌ እሰጣታለሁ፤ እሱም በእሳት ያቃጥላታል።+ 3 አንተም ከእጁ አታመልጥም፤ ያለጥርጥር ትያዛለህና፤ በእጁም አልፈህ ትሰጣለህ።+ የባቢሎንንም ንጉሥ በዓይኖችህ ታየዋለህ፤ ፊት ለፊትም ያነጋግርሃል፤ ወደ ባቢሎንም ትወሰዳለህ።’+ 4 ይሁንና የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ሆይ፣ የይሖዋን ቃል ስማ፤ ‘ይሖዋ ስለ አንተ እንዲህ ይላል፦ “በሰይፍ አትሞትም። 5 በሰላም ትሞታለህ፤+ ለአባቶችህ ይኸውም ከአንተ ቀድሞ ለነበሩት ነገሥታት እንዳደረጉት ለክብርህ እሳት ያነዱልሃል፤ ‘ወዮ፣ ጌታችን!’ እያሉም ያለቅሱልሃል፤ ‘እኔ ይህን ቃል ተናግሬአለሁና’ ይላል ይሖዋ።”’”’”

6 ከዚያም ነቢዩ ኤርምያስ በኢየሩሳሌም ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስ ይህን ሁሉ ቃል ነገረው፤ 7 በዚህ ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት ኢየሩሳሌምንና የቀሩትን የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ይኸውም ለኪሶንና+ አዜቃን+ እየወጋ ነበር፤+ ከይሁዳ ከተሞች መካከል ድል ሳይደረጉ የቀሩት እነዚህ የተመሸጉ ከተሞች ብቻ ነበሩና።

8 ንጉሥ ሴዴቅያስ ነፃነት ለማወጅ+ በኢየሩሳሌም ከነበረው ሕዝብ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን ከገባ በኋላ የይሖዋ ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ፤ 9 ቃል ኪዳኑ፣ እያንዳንዱ ሰው ዕብራውያን የሆኑ ወንድና ሴት ባሪያዎቹን በነፃ እንዲለቅ፣ ደግሞም ማንኛውም ሰው ወገኑ የሆነውን አይሁዳዊ፣ ባሪያው አድርጎ እንዳያሠራ የሚያዝዝ ነበር። 10 በመሆኑም መኳንንቱና ሕዝቡ ሁሉ እንደተባሉት አደረጉ። እያንዳንዳቸው ወንድና ሴት ባሪያዎቻቸውን በነፃ ለመልቀቅና ከዚያ በኋላ ባሪያ አድርገው ላለማሠራት ቃል ኪዳን ገቡ። እንደተባሉት በማድረግ ባሪያዎቻቸውን አሰናበቷቸው። 11 በኋላ ግን ነፃ ለቀዋቸው የነበሩትን ወንድና ሴት ባሪያዎቻቸውን መለሷቸው፤ እንደገናም አስገድደው በባርነት ገዟቸው። 12 ስለዚህ የይሖዋ ቃል ከይሖዋ ዘንድ እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦

13 “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አባቶቻችሁን ከግብፅ ምድር፣ ከባርነት ቤት ባወጣኋቸው ጊዜ+ እንዲህ ስል ከእነሱ ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ፦+ 14 “እያንዳንዳችሁ የተሸጠላችሁንና ስድስት ዓመት ሲያገለግላችሁ የቆየውን ዕብራዊ የሆነውን ወንድማችሁን በሰባተኛው ዓመት ማብቂያ ላይ ልቀቁት፤ በነፃ ልታሰናብቱት ይገባል።”+ አባቶቻችሁ ግን አልሰሙኝም ወይም ጆሯቸውን አልሰጡኝም። 15 እናንተም በቅርቡ* ተመልሳችሁ ለወገኖቻችሁ ነፃነት በማወጅ በፊቴ ትክክል የሆነውን ነገር አደረጋችሁ፤ ስሜ በተጠራበትም ቤት በፊቴ ቃል ኪዳን ገባችሁ። 16 በኋላ ግን ሐሳባችሁን ቀይራችሁ፣ እንደ ፍላጎታቸው* በነፃ የለቀቃችኋቸውን ወንድና ሴት ባሪያዎቻችሁን መልሳችሁ በማምጣት ስሜን አረከሳችሁ፤+ አስገድዳችሁም ወደ ባርነት መለሳችኋቸው።’

17 “ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እያንዳንዳችሁ ለወንድማችሁና ለወገናችሁ ነፃነት በማወጅ አልታዘዛችሁኝም።+ በመሆኑም እኔ ለእናንተ ያወጅኩት ነፃነት ይህ ነው’ ይላል ይሖዋ፤ ‘በሰይፍ፣ በቸነፈርና* በረሃብ ታልቃላችሁ፤+ ለምድር መንግሥታትም ሁሉ መቀጣጫ አደርጋችኋለሁ።+ 18 ጥጃውን ሁለት ቦታ ከፍለው በመካከሉ ባለፉ ጊዜ በፊቴ የገቡትን ቃል ኪዳን+ ባለማክበር ቃል ኪዳኔን የጣሱት ሰዎች የሚደርስባቸው ነገር ይህ ነው፤ 19 ይኸውም የይሁዳ መኳንንት፣ የኢየሩሳሌም መኳንንት፣ የቤተ መንግሥቱ ባለሥልጣናት፣ ካህናቱና ለሁለት በተከፈለው ጥጃ መካከል ያለፈው የምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ ይህ ነገር ይደርስባቸዋል፦ 20 ለጠላቶቻቸውና ሕይወታቸውን ማጥፋት ለሚሹ* ሰዎች አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።+ 21 የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስንና መኳንንቱን ሁሉ ለጠላቶቻቸው፣ ሕይወታቸውን ማጥፋት ለሚሹ* ሰዎችና እናንተን መውጋት ትቶ ለተመለሰው+ የባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት አሳልፌ እሰጣለሁ።’+

22 “‘እነሆ፣ እኔ ይህን ትእዛዝ አስተላልፋለሁ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘እነሱንም ወደዚህች ከተማ መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ እነሱም ይወጓታል፣ ይይዟታል፣ በእሳትም ያቃጥሏታል፤+ የይሁዳንም ከተሞች ማንም የማይኖርበት ጠፍ መሬት አደርጋቸዋለሁ።’”+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ