ኤርምያስ 21:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 “‘“መልካም ነገር ሳይሆን ጥፋት ለማምጣት ፊቴን ወደዚህች ከተማ አዙሬአለሁና”+ ይላል ይሖዋ። “ለባቢሎን ንጉሥ ትሰጣለች፤+ እሱም በእሳት ያቃጥላታል።”+ ኤርምያስ 32:28, 29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ይህችን ከተማ ለከለዳውያንና ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾር* እሰጣታለሁ፤ እሱም ይይዛታል።+ 29 ይህችን ከተማ የሚወጓት ከለዳውያንም ይገባሉ፤ በእሳትም ያቃጥሏታል፤+ ደግሞም ከተማዋን እንዲሁም ሕዝቡ እኔን ለማስቆጣት ሲሉ በጣሪያዎቻቸው ላይ ለባአል መሥዋዕቶች ያቀረቡባቸውንና ለሌሎች አማልክት የመጠጥ መባ ያፈሰሱባቸውን ቤቶች+ በእሳት ያቃጥሏቸዋል።’ ኤርምያስ 39:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ከለዳውያንም የንጉሡን ቤትና* የሕዝቡን ቤቶች አቃጠሉ፤+ የኢየሩሳሌምንም ቅጥሮች አፈረሱ።+
28 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ይህችን ከተማ ለከለዳውያንና ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾር* እሰጣታለሁ፤ እሱም ይይዛታል።+ 29 ይህችን ከተማ የሚወጓት ከለዳውያንም ይገባሉ፤ በእሳትም ያቃጥሏታል፤+ ደግሞም ከተማዋን እንዲሁም ሕዝቡ እኔን ለማስቆጣት ሲሉ በጣሪያዎቻቸው ላይ ለባአል መሥዋዕቶች ያቀረቡባቸውንና ለሌሎች አማልክት የመጠጥ መባ ያፈሰሱባቸውን ቤቶች+ በእሳት ያቃጥሏቸዋል።’